Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘፀአት 38:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 በምዕራብ በኩል አምሳ ክንድ ርዝመት ያላቸው መጋረጃዎች ነበሩ፤ ዐሥር ምሰሶዎችና ዐሥር የነሐስ እግሮች ነበሩት፥ የምሰሶዎቹ ኩላቦችና ዘንጎች ከብር የተሰሩ ነበሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 የምዕራቡ ጫፍ ወርዱ ዐምሳ ክንድ ነበር፤ ዐሥር ምሰሶዎችና ዐሥር መቆሚያዎች እንዲሁም የብር ኵላቦችና በምሰሶዎቹም ላይ ዘንጎች ያሉት መጋረጃዎች ነበሩት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 በምዕራብ በኩል ኻያ ሁለት ሜትር ርዝመት ያላቸው መጋረጃዎች ነበሩ፤ እነርሱም ዐሥር እግሮች ያሉአቸው ዐሥር ምሰሶዎች ነበሩአቸው፤ ምሰሶዎቹም ከብር የተሠሩ ኩላቦችና ዘንጎች ነበሩአቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 በም​ዕ​ራ​ብም ወገን አምሳ ክንድ ርዝ​መት ያላ​ቸ​ውን መጋ​ረ​ጃ​ዎች፥ ዐሥ​ሩ​ንም ምሰ​ሶ​ዎች፥ ዐሥ​ሩ​ንም የናስ እግ​ሮች፥ ለም​ሰ​ሶ​ዎ​ቹም የብር ኵላ​ቦ​ች​ንና ዘን​ጎ​ችን አደ​ረገ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 በምዕራብም ወገን አምሳ ክንድ ርዝመት ያላቸውን መጋረጆች፥ አሥሩንም ምሰሶች፥ አሥሩንም የናስ እግሮች፥ ለምሰሶቹም የብር ኩላቦችንና ዘንጎችን አደረገ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፀአት 38:12
3 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሀያ ምሰሶዎቹና ሀያ እግሮቹ ከነሐስ የተሠሩ ይሁኑ፤ የምሶሶቹ ኩላቦችና ዘንጎች ከብር የተሠሩ ይሁኑ።


በሰሜን በኩል መቶ ክንድ ርዝመት ያላቸውን መጋረጃዎች፥ ምሰሶዎቻቸው ሃያ የነሐስ እግሮቻቸውም ሃያ ነበሩ፥ የምሰሶዎቹ ኩላቦችና ዘንጎች ከብር የተሰሩ ነበሩ።


በምሥራቅም በኩል አምሳ ክንድ ርዝመት ያላቸው መጋረጃዎች ነበሩ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች