Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘፀአት 38:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 የሚቃጠል መሥዋዕት መሠዊያ ከግራር እንጨት ሠራ፤ እርሱም ርዝመቱ አምስት ክንድ፥ ወርዱ አምስት ክንድ ነበር፥ አራት ማዕዘንም ነበረ፥ ከፍታው ሦስት ክንድ ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ከፍታው ሦስት ክንድ የሆነ የሚቃጠል መሥዋዕት መሠዊያ ከግራር ዕንጨት ሠሩ፤ ርዝመቱ ዐምስት ክንድ፣ ወርዱ ዐምስት ክንድ የሆነ ባለአራት ማእዘን ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 የሚቃጠል መሥዋዕት መሠዊያ ከግራር እንጨት ሠራ፤ እርሱም አራት ማእዘን ሆኖ ሁለት ሜትር ከኻያ ሳንቲ ሜትር ርዝመት፥ ሁለት ሜትር ከኻያ ሳንቲ ሜትር ስፋት፥ አንድ ሜትር ከሠላሳ ሳንቲ ሜትር ቁመት ነበረው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ርዝ​መቱ አም​ስት ክንድ፥ ወር​ዱም አም​ስት ክንድ ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ሆን መሠ​ዊ​ያን ከማ​ይ​ነ​ቅዝ ዕን​ጨት አደ​ረገ፤ አራት ማዕ​ዘ​ንም ነበረ፤ ከፍ​ታ​ውም ሦስት ክንድ ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ርዝመቱ አምስት ክንድ፥ ወርዱም አምስት ክንድ ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚሆን መሠዊያን ከግራር እንጨት አደረገ፤ አራት ማዕዘንም ነበረ፤ ከፍታው ሦስት ክንድ ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፀአት 38:1
19 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የሆርም ልጅ የኡሪ ልጅ ባስልኤል የሠራው የናስ መሠዊያ በዚያ በጌታ ማደሪያ ፊት ነበረ፤ ሰሎሞንም ጉባኤውም ይህን ይፈልጉት ነበር።


ንጉሥ ሰሎሞንም ርዝመቱ ሀያ ክንድ፥ ወርዱም ሀያ ክንድ፥ ቁመቱም ዐሥር ክንድ የነበረውን የናሱን መሠዊያ ሠራ።


ቀይ የተለፋ የአውራ በግ ቁርበት፥ የአስቆጣ ቁርበት፥ የግራር እንጨት፥


ጌታ ሙሴን እንዲህ አለው፦


የሚቃጠል መሥዋዕት መሠዊያና ዕቃውን ሁሉ፥ የመታጠቢያ ሳሕንና መቀመጫውን፥


በአራቱም ማዕዘን ቀንዶችን አደረገበት፤ ቀንዶቹም ከእርሱ ጋር ወጥ ሆነው የተሠሩ ነበሩ፤ በነሐስም ለበጠው።


ጌታ ሙሴን እንዳዘዘው የሚቃጠል መሥዋዕት መሠዊያውን በመገናኛው ድንኳን በማደሪያው መግቢያ ፊት አኖረ፥ የሚቃጠልና የእህልን መሥዋዕት ሠዋበት።


የሚቃጠል መሥዋዕት መሠዊያውን በመገናኛው ድንኳን በማደሪያው መግቢያ ፊት ታኖረዋለህ።


አብ የሚሰጠኝ ሁሉ ወደ እኔ ይመጣል፤ ወደ እኔም የሚመጣውን ከቶ ወደ ውጭ አላስወጣውም፤


እንግዲህ ወንድሞች ሆይ! ሰውነታችሁን ሕያው መሥዋዕት፥ ቅዱስና እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ አድርጋችሁ እንድታቀርቡ በእግዚአብሔር ርኅራኄ እለምናችኋለሁ፤ ይህም መንፈሳዊ አገልግሎታችሁ ነው።


መሠዊያ አለን፤ ሆኖም ድንኳኒቱን የሚያገለግሉ ከእርሱ የመብላት መብት የላቸውም።


ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንትና፥ ዛሬም ለዘለዓለምም ያው ነው።


ስለዚህ ከሰማያዊው ጥሪ ተካፋዮች የሆናችሁ ቅዱሳን ወንድሞች ሆይ! የሃይማኖታችንን ሐዋርያና ሊቀ ካህናት ኢየሱስ ክርስቶስን ተመልከቱ፤


ነውር የሌለው ሆኖ በዘላለም መንፈስ ራሱን ለእግዚአብሔር ያቀረበው የክርስቶስ ደም እንዴት ልቆ፥ ሕያው እግዚአብሔርን ለማምለክ፥ ከሞተ ሥራ ሕሊናችሁን ያነጻ ይሆን!


እናንተ ደግሞ እንደ ሕያዋን ድንጋዮች ሆናችሁ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መሥዋዕትን ለማቅረብ፥ ቅዱሳን ካህናት እንድትሆኑ፥ መንፈሳዊ ቤት ለመሆን ተሠሩ።


ከተማይቱም አራት ማዕዘን ነበራት፤ ርዝመትዋም እንደ ስፋትዋ ልክ ነበረ። ከተማይቱንም በዘንግ ለካት፤ ሁለት ሺህ አራት መቶ ኪሎ ሜትር ሆነች፤ ርዝመትዋና ስፋትዋ ከፍታዋም ትክክል ነው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች