ዘፀአት 37:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)16 በገበታው ላይ የሚኖሩትን ዕቃዎች፥ ወጭቶቹን፥ ጭልፋዎችን፥ ጽዋዎችንና ለማፍሰሻ የሚሆኑ መቅጃዎችን፥ ከንጹሕ ወርቅ ሠራ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም16 የጠረጴዛውን ዕቃዎች ይኸውም ዝርግ ሳሕኖችን፣ ድስቶችንና ጐድጓዳ ሳሕኖችን እንዲሁም የመጠጥ መሥዋዕቱ ማፍሰሻ የሆኑትን ማንቈርቈሪያዎች ከንጹሕ ወርቅ ሠሯቸው። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም16 በጠረጴዛው ላይ የሚቀመጡ ልዩ ልዩ የመገልገያ ዕቃዎችን ከንጹሕ ወርቅ ሠራ፤ ይኸውም፦ የዕጣን ማስቀመጫ ዝርግ ሳሕኖችንና ወጭቶችን፥ ጭልፋዎችን ለወይን ጠጅ መቅጃ የሚሆኑ ማንቈርቈሪያዎችንና ጐድጓዳ ሣሕኖችን ሠራ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)16 ለማፍሰሻም ይሆኑ ዘንድ በገበታው ላይ የሚኖሩትን ዕቃዎች፥ ወጭቶቹንና ጭልፋዎቹን፥ ጽዋዎቹንም፥ መቅጃዎቹንም ከጥሩ ወርቅ አደረጋቸው። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)16 ለማፍሰሻም ይሆኑ ዘንድ በገበታው ላይ የሚኖሩትን ዕቃዎች፥ ወጭቶቹንና ጭልፋዎቹን ጽዋዎቹንም መቅጃዎቹንም፥ ከጥሩ ወርቅ አደረጋቸው። ምዕራፉን ተመልከት |