ዘፀአት 36:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)1 ባስልኤል፥ ኤልያብና ጥበበኞች ሁሉ፥ የመቅደሱን አገልግሎት ሥራ ሁሉ እንዲያደርጉና እንዲያውቁ ጌታ ጥበብንና ማስተዋልን የሰጣቸው ጌታ ያዘዘውን ነገር ሁሉ አደረጉ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም1 ስለዚህ የመቅደሱን የግንባታ ሥራ ሁሉ እንዴት ማከናወን እንዳለባቸው እግዚአብሔር ጥበብንና ችሎታን የሰጣቸው፣ ባስልኤል፣ ኤልያብና ጥበበኛ የሆኑ ሰዎች ሁሉ ሥራውን ልክ እግዚአብሔር እንዳዘዘው ይሥሩት።” ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም1 “ባጽልኤልና ኦሆሊአብ እንዲሁም ለተቀደሰው ድንኳን ዝግጅት እግዚአብሔር ማናቸውንም ሥራ ለመሥራት ችሎታንና ዕውቀትን የሰጣቸው ሌሎች ሰዎች እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት ይሠራሉ።” ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)1 “ባስልኤልና ኤልያብ፥ ለመቅደስም ማገልገያ ሥራ ሁሉ ያደርጉ ዘንድ እንዲያውቁ እግዚአብሔር ጥበብንና ማስተዋልን የሰጣቸው በልባቸውም ጥበበኞች የሆኑ ሁሉ እግዚአብሔር ያዘዘውን ነገር ሁሉ አደረጉ።” ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)1 ለመቅደስም ማገልገያ ሥራ ሁሉ ያደርጉ ዘንድ እንዲያውቁ እግዚአብሔር ጥበብንና ማስተዋልን የሰጣቸው ባስልኤልና ኤልያብ በልባቸው ጥበበኞችም ሁሉ እግዚአብሔር እንዳዘዘው ነገር ሁሉ አደረጉ። ምዕራፉን ተመልከት |