ዘፀአት 34:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)24 አሕዛብን ከፊትህ አስወግዳለሁ፥ ድንበርህንም አሰፋለሁ፤ በጌታ አምላክህ ፊት ለመታየት በዓመት ሦስት ጊዜ ስትወጣ ማንም ምድርህን አይመኝም። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም24 አሕዛብን ከፊትህ አስወጣለሁ፤ ድንበርህን አሰፋለሁ፤ በዓመት ሦስት ጊዜ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት ለመቅረብ ስትወጣ፣ ምድርህን ማንም አይመኝም። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም24 አሕዛብን ሁሉ አስወግጄ ግዛታችሁን አሰፋለሁ፤ ስለዚህ በእነዚህ በሦስት በዓላት ወቅት ወደ እኔ ስትቀርቡ አገራችሁን ለመውረር የሚመኝ ማንም አይመጣም። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)24 አሕዛብን ከፊትህ በአወጣሁ ጊዜ ሀገርህን አሰፋለሁ፤ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊትም ለመታየት በዓመት ሦስት ጊዜ ስትወጣ ማንም ምድርህን አይመኝም። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)24 አሕዛብን ከፊትህ አወጣለሁ፥ አገርህንም አሰፋለሁ፤ በአምላክህም በእግዚአብሔር ፊት ለመታየት በዓመት ሦስት ጊዜ ስትወጣ ማንም ምድርህን አይመኝም። ምዕራፉን ተመልከት |