Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፀአት 33:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 በፊትህ መልአክ እልካለሁ፥ ከነዓናዊውን፥ አሞራዊውን፥ ኬጢያዊውን፥ ፌርዛዊውን፥ ኤዊያዊውንና ኢያቡሳዊውን አወጣልሃለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 መልአክን በፊትህ በመላክ፣ ከነዓናውያንን፣ አሞራውያንን፣ ኬጢያውያንን፣ ፌርዛውያንን፣ ኤዊያዊያንንና ኢያቡሳውያንን አስወጣለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ፊት ፊትህ እየሄደ የሚመራህ መልአክ እልካለሁ፤ ከነዓናውያንን፥ አሞራውያንን፥ ሒታውያንን፥ ፈሪዛውያንን፥ ሒዋውያንንና ኢያቡሳውያንን ከፊትህ አባርራለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 መል​አ​ኬ​ንም ከአ​ንተ ጋር በፊ​ትህ እል​ካ​ለሁ፤ ከነ​ዓ​ና​ዊ​ውን፥ አሞ​ሬ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ኬጤ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ፌር​ዜ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ጌር​ጌ​ሴ​ዎ​ና​ዊ​ውን፥ ኤዌ​ዎ​ና​ው​ዊ​ው​ንም፥ ኢያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም ያወ​ጣ​ቸ​ዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፀአት 33:2
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዮርዳኖስንም ተሻገራችሁ፥ ወደ ኢያሪኮም መጣችሁ፤ የኢያሪኮም ሰዎች፥ አሞራዊው፥ ፌርዛዊው፥ ከነዓናዊው፥ ኬጢያዊው፥ ጌርጌሳዊው፥ ኤዊያዊው፥ ኢያቡሳዊው ተዋጉአችሁ፤ አሳልፌም በእጃችሁ ሰጠኋቸው።


አሁንም ሂድ፥ ይህንንም ሕዝብ ወደ ነገርኩህ ስፍራ ምራ፤ እነሆ መልአኬ በፊትህ ይሄዳል፤ ነገር ግን በምጐበኝበት ቀን ኃጢአታቸውን በላያቸው ላይ አመጣባቸዋለሁ።”


“በመንገድ እንዲጠብቅህ፥ ወዳዘጋጀሁትም ስፍራ እንዲያስገባህ፥ እነሆ፥ እኔ መልአክን በፊትህ እልካለሁ።


ጌታ አምላካችሁ እነዚህን ሕዝቦች ጥቂት በጥቂት ከፊትህ ያስወጣቸዋል፤ የዱር አራዊት እንዳይበዙብህ፥ እነርሱን በአንድ ጊዜ ማጥፋት አይቻልህም።


ዛሬ የማዝዝህን ነገር ጠብቅ፤ እነሆ እኔ አሞራዊውን፥ ከነዓናዊውን፥ ኬጢያዊውን፥ ፌርዛዊውን፥ ኤዊያዊውንና ኢያቡሳዊውን በፊትህ አወጣለሁ።


ከግብጽም መከራ ወደ ከነዓናውያን ወደ ኬጢያውያንም ወደ አሞራውያንም ወደ ፌርዛውያንም ወደ ኤዊያውያንም ወደ ኢያቡሳውያንም አገር ወተትና ማር ወደምታፈስስ አገር አወጣችኋለሁ።’


ከግብፃውያን እጅ አድናቸው ዘንድ፥ ከዚያችም አገር ወደ መልካምና ሰፊ አገር፥ ወተትና ማር ወደምታፈስሰው አገር ወደ ከነዓናውያን፥ ሒቲያውያን፥ ኤሞራውያን፥ ፌርዛውያን፥ ሒዊያውያን፥ የቡሳውያንም ስፍራ አወጣቸው ዘንድ ወረድሁ።


ሙሴ ጌታን እንዲህ አለው፥ “እይ! አንተ ‘ይህን ሕዝብ አውጣ’ ብለኸኛል፥ ነገር ግን ከእኔ ጋር የምትልከውን አላስታወቅኸኝም። አንተም፦ ‘በስምህ አወቅሁህ፥ ደግሞም በእኔ ፊት ሞገስን አግኝተሃል’ ብለኸኝ ነበር።


አሕዛብን ከፊትህ አስወግዳለሁ፥ ድንበርህንም አሰፋለሁ፤ በጌታ አምላክህ ፊት ለመታየት በዓመት ሦስት ጊዜ ስትወጣ ማንም ምድርህን አይመኝም።


ኢያሱም እንዲህ አለ፦ “ሕያው አምላክ በመካከላችሁ እንደሆነ፥ እርሱም ከነዓናዊውን ኬጢያዊውንም ኤዊያዊውንም ፌርዛዊውንም ጌርጌሳዊውንም አሞራዊውንም ኢያቡሳዊውንም ከፊታችሁ ፈፅሞ እንደሚያሳድድ በዚህ ታውቃላችሁ።


በዚያም ቀን ከእነርሱ መካከል ደካማው እንደ ዳዊት እንዲሆን፥ የዳዊትም ቤት በፊታቸው እንደ እግዚአብሔር መልአክ እንደ ጌታ እንዲሆን፥ ጌታ በኢየሩሳሌም ለሚኖሩት መከታ ይሆናቸዋል።


ፌርዛውያንንም ራፋይምንም አሞራውያንንም ከነዓናውያንንም ጌርጌሳውያንንም ኢያቡሳውያንንም።”


ከአባቴ ቤት ከተወለድሁባት ምድርም ያወጣኝ፦ ‘ይህችንም ምድር ለዘርህ እሰጥሃለሁ’ ብሎ የነገረኝና የማለልኝ የሰማይ አምላክ እግዚአብሔር፥ እርሱ መልአኩን በፊትህ ይሰድዳል፥ ከዚያም ለልጄ ሚስትን ትወስዳለህ።


ከግብፃውያን እጅ ታደግኋችሁ፤ ከሚያስጨንቋችሁ ሁሉ አዳንኋችሁ፤ እነርሱንም ከፊታችሁ አሳድጄ አስወጣኋቸው፤ ምድራቸውንም ሰጠኋችሁ።”


ኢያቡሳዊውን፥ አሞራዊውን፥ ጌርጌሳዊውን፥


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች