ዘፀአት 33:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)19 እርሱም እንዲህ አለው፦ “እኔ መልካምነቴን ሁሉ በፊትህ አሳልፋለሁ የጌታንም ስም በፊትህ አውጃለሁ፤ ይቅር የምለውን ይቅር እላለሁ፥ የምምረውን እምራለሁ።” ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም19 እግዚአብሔር እንዲህ አለ፤ “መልካምነቴ ሁሉ በፊትህ እንዲያልፍ አደርጋለሁ፤ በፊትህም ስሜን እግዚአብሔርን ዐውጃለሁ፤ የምምረውን እምረዋለሁ፤ የምራራለትንም ራራለታለሁ፤ ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም19 እግዚአብሔርም እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “ደግነቴን ሁሉ በፊትህ አሳልፋለሁ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ስሜን በፊትህ ዐውጃለሁ፤ የምምረውን እምራለሁ፤ የምራራለትንም እራራለታለሁ፤ ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)19 እግዚአብሔርም፥ “እኔ በክብሬ በፊትህ አልፋለሁ፤ የእግዚአብሔርንም ስም በፊትህ እጠራለሁ፤ ይቅርም የምለውን ይቅር እላለሁ፤ የምምረውንም እምራለሁ” አለ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)19 እግዚአብሔርም፦ እኔ መልካምነቴን ሁሉ በፊትህ አሳልፋለሁ፤ የእግዚአብሔርንም ስም በፊትህ አውጃለሁ፤ ይቅርም የምለውን ይቅር እላለሁ፥ የምምረውንም እምራለሁ አለ። ምዕራፉን ተመልከት |