ዘፀአት 30:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)4 ከአክሊሉ በታች ሁለት የወርቅ ቀለበቶችን አድርግለት፤ በዚህና በዚያ በሁለቱ ጎን ታደርጋቸዋለህ፤ በእነርሱ እንዲሸከሙም የመሎጊያዎቹ ማስገቢያ ይሁኑ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም4 መሠዊያውን ለመሸከም የሚያገለግሉትን መሎጊያዎች የሚይዙ፣ ከክፈፉ በታች ትይዩ የሆኑ ሁለት የወርቅ ቀለበቶችን ለመሠዊያው አብጅ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም4 ሁለት የወርቅ ቀለበቶችን ሠርተህ መሠዊያውን ለመሸከም የሚያገለግሉት መሎጊያዎች እንዲገቡበት ከክፈፉ ሥር አያይዛቸው። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)4 ከክፈፉም በታች ሁለት የወርቅ ቀለበቶች አድርግለት። በዚህና በዚያ በሁለቱ ጐን ታደርጋቸዋለህ፤ እርሱን ያነሡባቸው ዘንድ የመሎጊያዎቹ መግቢያ ይሁኑ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)4 ከክፈፉም በታች ሁለት የወርቅ ቀለበቶች አድርግለት። በዚህና በዚያ በሁለቱ ጎን ታደርጋቸዋለህ፤ ለመሸከምም የመሎጊያዎች ስፍራ ይሁኑ። ምዕራፉን ተመልከት |