Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘፀአት 3:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ስለዚህ ሂድ፥ ሕዝቤን የእስራኤልን ልጆች ከግብጽ እንድታወጣ ወደ ፈርዖን እልክሃለሁ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 በል እንግዲህ ና፤ ሕዝቤን፣ የእስራኤልን ልጆች ከግብጽ ምድር እንድታወጣቸው ወደ ፈርዖን እልክሃለሁ”።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ስለዚህ አሁን ሕዝቤን ከግብጽ ምድር ታወጣ ዘንድ ወደ ግብጽ ንጉሥ እልክሃለሁ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 አሁ​ንም ና፤ ወደ ግብፅ ንጉሥ ወደ ፈር​ዖን እል​ክ​ሃ​ለሁ። ሕዝ​ቤን የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ከግ​ብፅ ምድር ታወ​ጣ​ቸ​ዋ​ለህ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 አሁንም ና! ሕዝቤን የእስራኤልን ልጆች ከግብፅ ታወጣ ዘንድ ወደ ፈርዖን እልክሃለሁ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፀአት 3:10
20 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አብራምንም አለው፦ “ዘርህ ለእርሱ ባልሆነች ምድር ስደተኞች እንደሚሆኑ በእርግጥ እወቅ፥ ባርያዎች አድርገውም አራት መቶ ዓመት ያስጨንቋቸዋል።


ደግሞም በባርነት በሚገዙአቸው ሕዝብ ላይ እኔ እፈርዳለሁ፥ ከዚያም በኋላ በብዙ ከብት ይወጣሉ።


አገልጋዩን ሙሴን የመረጠውንም አሮንን ላከ።


መንገድህ በባሕር ውስጥ ነው፥ ያለፍከውም ኃይለኛ ውኆች በኩል ነው፤ ዱካህ ግን አልታወቀም።


የእስራኤልም ልጆች በግብጽ የኖሩበት ጊዜ አራት መቶ ሠላሳ ዓመት ነበር።


እንዲህም ሆነ አራት መቶ ሠላሳ ዓመት ከተፈጸመ በኋላ በዚህ ቀን የጌታ ሠራዊት ሁሉ ከግብጽ ምድር ወጡ።


ሙሴ ጌታን እንዲህ አለው፥ “እይ! አንተ ‘ይህን ሕዝብ አውጣ’ ብለኸኛል፥ ነገር ግን ከእኔ ጋር የምትልከውን አላስታወቅኸኝም። አንተም፦ ‘በስምህ አወቅሁህ፥ ደግሞም በእኔ ፊት ሞገስን አግኝተሃል’ ብለኸኝ ነበር።


አሁንም በፊትህ ሞገስ አግኝቼ እንደሆነ፥ እንዳውቅህና በፊትህም ሞገስን እንዳገኝ እባክህ መንገድህን አሳየኝ፤ ይህንንም ሕዝብ እንደ ሕዝብህ እየው።”


እነዚህ አሮንና ሙሴ ጌታ፦ “የእስራኤልን ልጆች በየነገዳቸው ከግብጽ ምድር አውጡ” ያላቸው ናቸው።


ያዕቆብ ወደ አራም ምድር ሸሸ፥ እስራኤልም ስለ ሚስት አገለገለ፥ ስለ ሚስትም በጎችን ያሰማራ ነበረ።


ከግብጽ ምድር አውጥቼሃለሁ፥ ከባርነት ቤትም ተቤዥቼሃለሁና፤ በፊትህም ሙሴን፥ አሮንንና ማርያምን ላክሁልህ።


በግብጽ ያሉትን የሕዝቤን መከራ ፈጽሜ አይቼ መቃተታቸውንም ሰምቼ ላድናቸው ወረድሁ፤ አሁንም ና፤ ወደ ግብጽ እልክሃለሁ፤’ አለው።


ይህ ሰው በግብጽ ምድርና በኤርትራ ባሕር በምድረ በዳም አርባ ዓመት ድንቅና ምልክት እያደረገ አወጣቸው።


እግዚአብሔርም ዘሩ በሌላ አገር መጻተኞች እንዲሆኑ አራት መቶ ዓመትም ባርያዎች እንዲያደርጉአቸው እንዲያስጨንቁአቸውም እንዲህ ተናገረ፤


ደግሞም እግዚአብሔር ‘እንደ ባርያዎች በሚገዙአቸው ሕዝብ ላይ እኔ እፈርድባቸዋለሁ፤ ከዚህም በኋላ ይወጣሉ፤ በዚህም ስፍራ ያመልኩኛል፤’ አለ።


በዚህ ጊዜ ጌታ ወደ እርሱ ዘወር ብሎ፥ “ባለህ ኃይል ሂድ፤ እስራኤውያንን ከምድያማውያን እጅ ነጻ እንድታወጣ የምልክህ እኔ አይደለሁምን? አለው”


ከዚያም ሳሙኤል ለሕዝቡ እንዲህ አለ፤ “ሙሴንና አሮንን የመረጠ፥ የቀድሞ አባቶቻችሁንም ከግብጽ ያወጣ ጌታ ነው።


ያዕቆብ ወደ ግብጽ ከገባ በኋላ፥ አባቶቻችሁ ጌታ እንዲረዳቸው ወደ እርሱ ጮኹ፤ ጌታም የቀድሞ አባቶቻችሁን ከግብጽ ምድር አውጥተው በዚህ ስፍራ እንዲኖሩ ያደረጉትን ሙሴንና አሮንን ላከላቸው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች