Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፀአት 27:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 “የማደሪያውን አደባባይ ሥራ፤ በደቡብ በኩል ከጥሩ በፍታ የተሠሩ መጋረጃዎች ይሁኑ፥ የአንዱ ወገን ርዝመት መቶ ክንድ ይሁን፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 “ለመገናኛው ድንኳን አደባባይ አብጅለት፤ በደቡብ በኩል ርዝመቱ አንድ መቶ ክንድ ይሁን፤ ከቀጭን በፍታ የተፈተሉ መጋረጃዎች፣

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 “ለድንኳኑ አደባባይ ክልል መጋረጃዎች ከቀጭን ሐር ሥራ፤ የመጋረጃዎቹም ርዝመት ከደቡብ በኩል አርባ አራት ሜትር ይሁን፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 “ለድ​ን​ኳ​ኑም አደ​ባ​ባይ ሥራ፤ ከጥሩ በፍታ የተ​ሠሩ የአ​ደ​ባ​ባዩ መጋ​ረ​ጃ​ዎ​ችም በደ​ቡብ በኩል ይሁኑ። የአ​ን​ዱም ወገን ርዝ​መት መቶ ክንድ ይሁን፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 የማደሪያውንም አደባባይ ሥራ፤ በደቡብ ወገን የጥሩ በፍታ መጋረጆች ይሁኑለት፥ የአንዱም ወገን ርዝመት መቶ ክንድ ይሁን፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፀአት 27:9
29 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በውስጠኛው አደባባይ በሀያው ክንድ ፊት ለፊት በውጭውም አደባባይ በወለሉ ፊት ለፊት በሦስት ደርብ በትይዩ የተሠራ መተላለፊያ ነበረ።


በውስጠኛው መግቢያ በውጭው በኩል በውስጠኛው አደባባይ ለሚዘምሩ ዕቃ ቤቶች ነበሩ፤ አንዱ ወደ ሰሜን በሚመለከት በር አጠገብ ነበረ፥ ወደ ደቡብም ይመለከት ነበር፤ ሌላው ደግሞ ወደ ምሥራቅ በሚመለከተው በር አጠገብ ነበረ፥ ወደ ሰሜን ይመለከት ነበር።


በምሥራቅ በኩል ወዳለው ወደ ውስጠኛው አደባባይ አመጣኝ፥ በሩንም ለካው፤ መጠኑም ከሌሎቹ ጋር እኩል ነበር፤


በደቡብ በር በኩል ወዳለው ወደ ውስጠኛው አደባባይ አመጣኝ፤ የደቡብንም በር ለካ፤ ከሌሎቹ ጋር እኩል መጠን ነበረው።


በምሥራቁ በር እንዳለው ዓይነት በሰሜኑ በር ትይዩ ወደ ውስጠኛው አደባባይ የሚያስገባ በር ነበር፤ ከአንዱ በር እስከ ሌላው በር አንድ መቶ ክንድ አድርጎ ለካ።


በውጭው አደባባይ ያለ ወደ ሰሜን የሚመለከተውን በር ርዝመትና ወርዱን ለካ።


መተላለፊያውን ሀያ ክንድ አድርጎ ለካ፤ በበሩም መተላለፊያ ዙሪያ አደባባይ ነበረ።


በጌታ ቤት አደባባይ፥ ኢየሩሳሌም ሆይ፥ በመካከልሽም እንዲሁ። ሃሌ ሉያ።


ወደ ደጆቹ በውዳሴ፥ ወደ አደባባዮቹም በምስጋና ግቡ፥ አመስግኑት፥ ስሙንም ባርኩ፥


ጻድቅ እንደ ዘንባባ ያፈራል፥ እንደ ሊባኖስ ዝግባም ያድጋል።


አቤቱ፥ መታመናችንን እይልን፥ ወደ ቀባኸውም ፊት ተመልከት።


በጌታም ቤት በሁለቱ አደባባዮች ላይ ለሰማይ ሠራዊት ሁሉ መሠዊያዎችን ሠራ።


እንዲሁም በዚያኑ ቀን ከቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት ያለውን አደባባይ መካከለኛ ክፍል ለእግዚአብሔር የተለየ እንዲሆን አደረገ፤ ቀጥሎም በሙሉ የሚቃጠለውን መሥዋዕት፥ የእህል ቁርባንና የኅብረት መሥዋዕት፥ የእንስሶች ስብ ሁሉ ለእግዚአብሔር አቀረበ፤ ይህንንም ያደረገበት ምክንያት ከነሐስ የተሠራው መሠዊያ ይህን ሁሉ መሥዋዕት መያዝ ስለማይችል ነው።


በቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት አንድ የውስጥ አደባባይ ሠራ፤ በዚህም አደባባይ ዙሪያ በየሦስቱ ዙር የድንጋይ ረድፍ አንድ የሊባኖስ ዛፍ ሠረገላ ሳንቃ የተጋደመበት ግንብ አደረገ።


በዙሪያውም አደባባዩን ትተክላለህ፥ መጋረጃውንም በአደባባዩ ደጃፍ ትዘረጋለህ።


የአደባባዩን መጋረጃዎች፥ ምሰሶዎቹን፥ እግሮቹን፥ የአደባባዩን ደጃፍ መጋረጃ፥ አውታሮቹን፥ ካስማዎቹን፥ ለመገናኛው ድንኳን ለማደሪያው የመገልገያ ዕቃዎች ሁሉ፥


ከተጋጠሙት መጋረጃዎች በአንደኛው መጋረጃ ጠርዝ ላይ አምሳ ቀለበቶች አደረገ፤ እንዲሁም በሁለተኛው መጋረጃ ጠርዝ በሚጋጠሙበት በኩል አምሳ ቀለበቶች አደረገ።


ሀያ ምሰሶዎቹና ሀያ እግሮቹ ከነሐስ የተሠሩ ይሁኑ፤ የምሶሶቹ ኩላቦችና ዘንጎች ከብር የተሠሩ ይሁኑ።


የአደባባዩን መጋረጃዎች፥ ምሰሶዎቹንና እግሮቻቸውን፥ የአደባባዩን ደጃፍ መጋረጃ፤


በማደሪያውና በመሠዊያው ዙሪያ አደባባዩን ተከለ፤ በአደባባዩንም ደጃፍ መጋረጃ ዘረጋ። በዚህ ዓይነት ሙሴ ሥራውን ፈጸመ።


የአደባባዩንም መጋረጆች፥ በማደሪያውና በመሠዊያው ዙሪያ ያለው የአደባባዩን ደጃፍ መጋረጃ፥ ገመዶቹንም መገልገያውንም ሁሉ ይሆናል።


የአደባባዩንም መጋረጆች፥ በማደሪያውና በመሠዊያው ዙሪያ ያለውን የአደባባዩን ደጃፍ መግብያ መጋረጃ፥ አውታሮቻቸውንም፥ የሚገለገሉባቸውንም ዕቃዎች ሁሉ ይሸከማሉ፤ እነርሱንም በሚመለከት ሊደረግ የሚገባውን ነገር ሁሉ ያድርጋሉ።


በዙሪያውም የሚቆሙትን የአደባባዩ ምሰሶች፥ እግሮቻቸውንም፥ ካስማዎቻቸውንም፥ አውታሮቻቸውንም፥ ዕቃዎቻቸውንና በተጓዳኝ የሚደረጉላቸውን አገልግሎቶች ሁሉ ነው፤ መሸከምም ያለባቸውን ዕቃዎች በየስሙ ትደለድላላችሁ።


እንዲሁም የካህናቱን አደባባይ፥ ታላቁንም አደባባይ፥ የአደባባዩንም ደጆች ሠራ፥ ደጆቻቸውንም በናስ ለበጠ።


ከዚያም ወደ ውጪው አደባባይ አመጣኝ፥ እነሆ በአደባባዩ ዙሪያ የተሠሩ ዕቃ ቤቶችና ወለል ነበሩ፤ በወለሉም ላይ ሠላሳ ዕቃ ቤቶች ነበሩ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች