Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፀአት 27:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 “ርዝመቱ አምስት ክንድ፥ ወርዱ አምስት ክንድ የሆነ መሠዊያ ከግራር እንጨት ሥራ፤ መሠዊያው አራት ማዕዘን ይሁን፤ ከፍታው ሦስት ክንድ ይሁን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 “ከፍታው ሦስት ክንድ የሆነ መሠዊያ ከግራር ዕንጨት ሥራ፤ ርዝመቱ ዐምስት፣ ወርዱም ዐምስት ክንድ ሆኖ ባለአራት ማእዘን ይሁን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 “ከግራር እንጨት መሠዊያ ሥራ፤ ርዝመቱ ሁለት ሜትር ከኻያ ሳንቲ ሜትር የጐኑ ስፋት ሁለት ሜትር ከኻያ ሳንቲ ሜትር ቁመቱም አንድ ሜትር ከሠላሳ ሳንቲ ሜትር ይሁን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 “ርዝ​መቱ አም​ስት ክንድ፥ ወር​ዱም አም​ስት ክንድ መሠ​ዊ​ያን ከማ​ይ​ነ​ቅዝ ዕን​ጨት አድ​ርግ፤ አራት ማዕ​ዘ​ንም ይሁን፤ ከፍ​ታ​ውም ሦስት ክንድ ይሁን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ርዝመቱ አምስት ክንድ፥ ወርዱም አምስት ክንድ መሠዊያ ከግራር እንጨት አድርግ፤ አራት ማዕዘንም ይሁን፤ ከፍታውም ሦስት ክንድ ይሁን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፀአት 27:1
20 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

መሠዊያ አለን፤ ሆኖም ድንኳኒቱን የሚያገለግሉ ከእርሱ የመብላት መብት የላቸውም።


ንጉሥ ሰሎሞንም ርዝመቱ ሀያ ክንድ፥ ወርዱም ሀያ ክንድ፥ ቁመቱም ዐሥር ክንድ የነበረውን የናሱን መሠዊያ ሠራ።


በዚያን ቀን ጋድ ወደ ዳዊት መጥቶ፥ “ውጣና በኢያቡሳዊው በኦርና ዐውድማ ላይ ለጌታ መሠዊያ ሥራ” አለው።


ጌታ ሙሴን እንዳዘዘው የሚቃጠል መሥዋዕት መሠዊያውን በመገናኛው ድንኳን በማደሪያው መግቢያ ፊት አኖረ፥ የሚቃጠልና የእህልን መሥዋዕት ሠዋበት።


የሚቃጠል መሥዋዕት መሠዊያውንና ዕቃዎቹን ሁሉ ትቀባለህ፥ መሠዊያውንም ትቀድሳለህ፤ መሠዊያውም እጅግ የተቀደሰ ይሆናል።


ሙሴም የጌታን ቃሎች ሁሉ ጻፈ፤ በማለዳ ተነሥቶ ከተራራው በታች መሠዊያንና ዐሥራ ሁለት ሐውልቶች ለዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገድ ሠራ።


የሚቃጠል መሥዋዕት መሠዊያና የነሐሱን መከታ፥ መሎጊያዎቹንና ዕቃውን ሁሉ፥ የመታጠቢያውን ሳሕንና ማስቀመጫውን፤


ታቦቱንም፥ ገበታውንም፥ መቅረዙንም፥ መሠዊያዎቹንም፥ ካህናቱም የሚገለገሉባቸውን የመቅደሱን ዕቃዎች፥ መጋረጃውንም፥ መገልገያውንም ሁሉ ይጠብቃሉ።


አመዱንም ከመሠዊያው ላይ ያስወግዱ፥ ሐምራዊውንም መጐናጸፊያ ይዘርጉበት፤


ከነሐስ ተሠርቶ ለእግዚአብሔር የተለየውም መሠዊያ በዚያ አዲስ መሠዊያና በቤተ መቅደሱ መካከል ነበር፤ አካዝም ያንን መሠዊያ አስነሥቶ እርሱ ባሠራው በአዲሱ መሠዊያ በስተ ሰሜን በኩል አኖረው፤


አሮንና ልጆቹ ግን የእግዚአሔር ባርያ ሙሴ እንዳዘዘው ሁሉ ለቅድስተ ቅዱሳን ሥራ ሁሉ ስለ እስራኤልም ለማስተስረይ ለሚቃጠለው መሥዋዕት በሚሆነው መሠዊያ ላይ ይሠዉ ነበር፥ በዕጣኑም መሠዊያ ላይ ያጥኑ ነበር።


የዮፃዳቅም ልጅ ኢያሱ ተነሣ፥ ወንድሞቹ ካህናትና፥ የሸአልቲኤል ልጅ ዘሩባቤልና ወንድሞቹም በእግዚአብሔር ሰው በሙሴ ሕግ እንደ ተጻፈ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ሊያቀርቡበት የእስራኤልን አምላክ መሠዊያ ሠሩ።


ሙሴም መሠዊያ ሠራ፥ ስሙንም “ጌታ ሰንደቅ ዓላማዬ ነው” ብሎ ጠራው፤


የሚቃጠል መሥዋዕት መሠዊያና ዕቃውን ሁሉ፥ የመታጠቢያ ሳሕንና መቀመጫውን፥


የናሱን መሠዊያ፥ የናሱን መከታ፥ መሎጊያዎቹንና ዕቃዎቹን ሁሉ፥ የመታጠቢያውን ሳሕንና ማስቀመጫው፥


የሚቃጠል መሥዋዕት መሠዊያውን በመገናኛው ድንኳን በማደሪያው መግቢያ ፊት ታኖረዋለህ።


በእርሱም ላይ የሚገለገሉባቸውን የመሠውያውን ዕቃዎች ሁሉ፥ ጀሞዎቹን ሜንጦቹንም መጫሪያዎቹንም ጐድጓዳ ሳሕኖቹንም፥ የመሠዊያውን ዕቃ ሁሉ ያስቀምጡበት፤ በእርሱም ላይ የአቆስጣን ቁርበት መሸፈኛ ይዘርጉ፥ መሎጊያዎቹንም ያግቡ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች