Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘፀአት 26:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ከማደሪያውም በላይ ለመሸፈኛ የሚሆኑ መጋረጆች ከፍየል ጠጉር ሥራ፤ ዐሥራ አንድ መጋረጆች ትሠራለህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 “ማደሪያ ድንኳኑን ከላይ ሆነው የሚሸፍኑ በጠቅላላ ዐሥራ አንድ የፍየል ጠጕር መጋረጃዎች ሥራ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 “ከፍየል ጠጒር የተሠሩ ዐሥራ አንድ መጋረጃዎችን ለድንኳኑ ክዳን አድርግ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 “ከማ​ደ​ሪ​ያ​ውም በላይ ለድ​ን​ኳን የሚ​ሆኑ መጋ​ረ​ጃ​ዎች ከፍ​የል ጠጕር አድ​ርግ፤ ዐሥራ አንድ መጋ​ረ​ጃ​ዎች ታደ​ር​ጋ​ለህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ከማደሪያውም በላይ ለድንኳን የሚሆኑ መጋረጆች ከፍየል ጠጉር አድርግ፤ አሥራ አንድ መጋረጆች ታደርጋለህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፀአት 26:7
18 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የጢሮስ ሴት ልጅ፥ የምድር ባለ ጠጎች አሕዛብ በፊትሽ ደጅ ይጠናሉ።


ሰማያዊ፥ ሐምራዊ፥ ቀይ ግምጃ፥ ጥሩ በፍታና የፍየል ጠጉር፥


“ከተፈተለ ከጥሩ በፍታ፥ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊና ከቀይ ግምጃ የተሠሩ ዐሥር መጋረጆች ያሉበትን ድንኳን ሥራ፤ ብልህ ሠራተኛ እንደሚሠራ ኪሩቤል በእነርሱ ላይ ይሁኑ።


ከድንኳኑ መጋረጆች የቀረ ትርፍ ግማሽ መጋረጃ በማደሪያው ጀርባ ይንጠልጠል።


ለድንኳኑም መደረቢያ ከቀይ አውራ በግ ቁርበት፥ ከዚያም በላይ ሌላ መደረቢያ ከአስቆጣ ቁርበት አድርግ።


አምሳ የወርቅ መያዣዎችን ሥራ፤ ድንኳኑም አንድ ወጥ እንዲሆን መጋረጃዎቹን እርስ በርሳቸው በመያዣዎች አጋጥማቸው።


የእያንዳንዱ መጋረጃ ርዝመቱ ሠላሳ ክንድ፥ የእያንዳንዱም መጋረጃ ወርድ አራት ክንድ ይሁን፤ የዐሥራ አንዱም መጋረጆች መጠን እኩል ይሁን።


አምስቱን መጋረጆች ለብቻ፥ ስድስቱንም መጋረጆች ለብቻ አንድ ሆነው ይጋጠሙ፤ ስድስተኛው መጋረጃ በድንኳኑ ፊት ይደረብ።


ሰማያዊ፥ ሐምራዊ፥ ቀይ ግምጃ፥ ጥሩ በፍታ፥ የፍየል ጠጉር፥ ቀይ የአውራ በግ ቁርበት፥ የአቆስጣ ቁርበት ያላቸው ሰዎች ሁሉ አመጡ።


ልባቸው በጥበብ ያነሣሣቸው ሴቶች ሁሉ የፍየልን ጠጉር ፈተሉ።


ሰማያዊ፥ ሐምራዊና ቀይ ግምጃ፥ ጥሩ በፍታ፥ የፍየል ጠጉር፥


ከዚያም ጌታ በጽዮን ተራራ ላይና በዚያ በሚሰበሰቡትም ሁሉ ላይ በቀን ደመናንና ጢስን፤ በሌሊትም የሚንበለበለውን የእሳት ብርሃን ይፈጥራል፤ በክብሩ ሁሉ ላይ መጋረጃ ይሆናል፤


ጌድሶናውያንም በመገናኛው ድንኳን የሚጠብቁት ማደሪያውን፥ ድንኳኑን፥ መደረቢያውን፥ የመገናኛውንም ድንኳን ደጃፍ መጋረጃ፥


ልብስንም፥ ከቁርበትም የተዘጋጀውን ሁሉ፥ ከፍየልም ጠጉር ከእንጨትም የተሠራውን ሁሉ አንጹ።”


የማደሪያውን መጋረጆች፥ የመገናኛውንም ድንኳን፥ መደረቢያውን፥ በእርሱም ላይ ያለውን የአቆስጣውን ቁርበት መሸፈኛ፥ የመገናኛውንም ድንኳን ደጃፍ መጋረጃ፥


ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ዋጋው እጅግ በከበረና በማይጠፋው ጌጥ በገርነትና በጽሞና መንፈስ የተዋበው የተሰወረ ውስጣዊ ሰውነት ይሁን።


እንዲሁም እናንተ ጐልማሶች! ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም ትሕትናን እንደ ልብስ ለብሳችሁ አንዱ ሌላውን ያገልግል፤ “እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፤ ለትሑታኑ ግን ጸጋን ይሰጣል” ተብሎ ተጽፎአልና።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች