ዘፀአት 24:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)3 ሙሴም መጣ ለሕዝቡም የጌታ ቃሎች ሁሉ ሥርዓቱንም ሁሉ ነገረ፤ ሕዝቡም ሁሉ በአንድ ድምፅ፦ “ጌታ የተናገራቸውን ቃሎች ሁሉ እናደርጋለን” ብለው መለሱ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም3 ሙሴ ወደ ሕዝቡ ሄዶ የእግዚአብሔርን ቃሎችና ሕጎች ሁሉ በነገራቸው ጊዜ በአንድ ድምፅ ሆነው፣ “እግዚአብሔር ያለውን ሁሉ እናደርጋለን” አሉ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም3 ሙሴም ሄዶ የእግዚአብሔርን ትእዛዝና ሥርዓት ሁሉ ለሕዝቡ ነገረ፤ ሕዝቡም በአንድነት “እግዚአብሔር የተናገረውን ሁሉ እናደርጋለን” ሲል መለሰ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)3 ሙሴም ገባ፤ ለሕዝቡም የእግዚአብሔርን ቃሎች ሁሉ፥ ሥርዐቱንም ሁሉ ነገረ፤ ሕዝቡም ሁሉ በአንድ ድምፅ፥ “እግዚአብሔር የተናገራቸውን ቃሎች ሁሉ እንሰማለን፤ እናደርጋለንም” ብለው መለሱ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)3 ሙሴም መጣ ለሕዝቡም የእግዚአብሔርን ቃሎች ሁሉ ሥርዓቱንም ሁሉ ነገረ፤ ሕዝቡም ሁሉ በአንድ ድምፅ፦ እግዚአብሔር የተናገራቸውን ቃሎች ሁሉ እናደርጋለን ብለው መለሱ። ምዕራፉን ተመልከት |