ዘፀአት 22:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)9 አንድ ሰው ለባልንጀራው አህያ ወይም በሬ ወይም በግ ወይም ሌላ እንስሳ እንዲጠብቅለት በአደራ ቢሰጥ፥ ማንም ሳያይ ቢሞት ወይም ቢጎዳ ወይም ቢማረክ፥ ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም9 አንድ ሰው በሬን፣ አህያን፣ በግን፣ ልብስን ወይም ማንኛውንም ንብረት ያለ አግባብ በባለቤትነት ይዞ ሳለ፣ ‘የእኔ ነው’ ባይ ቢመጣና ክርክር ቢነሣ፣ ባለጕዳዮቹ ነገሩን ለዳኞች ያቅርቡት፤ ዳኞቹ ጥፋተኛ ነው ያሉትም ለጎረቤቱ ዕጥፉን ይክፈል። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም9 “ስለ ከብት፥ ስለ አህያ፥ ስለ በግ ስለ ልብስና ወይም ስለ ማንኛውም የጠፋ ዕቃ ሁለት ሰዎች ቢካሰሱ፥ ስለ ንብረቱ ባለቤትነት የተጣሉት ሁለቱ ሰዎች የእግዚአብሔር አገልጋዮች በሆኑ ዳኞች ፊት ይቅረቡ፤ እግዚአብሔር በደሉን በዳኞቹ አማካይነት የሚገለጥበት ሰው፥ ለተበደለው ሰው ዕጥፍ አድርጎ ይክፈል። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)9 ሰዎች ስለ በሬ ወይም ስለ አህያ ወይም ስለ በግ ወይም ስለ ልብስ ወይም ስለሌላ ስለ ጠፋ ነገር ቢካሰሱ፥ አንዱም፦ ‘ይህ የእኔ ነው’ ቢል፥ ክርክራቸው በፈጣሪ ፊት ይቅረብ፤ በፈጣሪ ፊት የተፈረደበት እርሱ ለባልንጀራው እጥፍ ይክፈል። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)9 ሰዎች ስለ በሬ ወይም ስለ አህያ ወይም ስለ በግ ወይም ስለ ልብስ ወይም ስለ ሌላ ስለ ጠፋ ነገር ቢካሰሱ፥ አንዱም፦ ይህ የእኔ ነው ቢል፥ ክርክራቸው ወደ ፈራጆች ይድረስ፤ ፈራጆቹም የፈረዱበት እርሱ ለባልንጀራው በአንድ ሁሉት ይክፈል። ምዕራፉን ተመልከት |