Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፀአት 22:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ሰዎች ስለ በሬ ወይም ስለ አህያ ወይም ስለ በግ ወይም ስለ ልብስ ወይም ስለ ሌላ ስለ ጠፋ ነገር ቢካሰሱ፥ አንዱም፦ ይህ የእኔ ነው ቢል ክርክራቸው ወደ እግዚአብሔር ይምጣ፤ እግዚአብሔርም የፈረደበት እርሱ ለባልንጀራው እጥፍ አድርጎ ይክፈል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ሌባው ካልተያዘ ግን፣ የቤቱ ባለቤት በንብረቱ ስርቆት ላይ እጁ ይኑርበት ወይም አይኑርበት ይታወቅ ዘንድ ዳኞች ፊት ይቅረብ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ሌባው ካልተገኘ ግን ዕቃውን በዐደራ የተቀበለው ሰው የእግዚአብሔር አገልጋዮች በሆኑ ዳኞች ፊት ቀርቦ የዚያን ሰው ንብረት አለመስረቁን በመሐላ ያረጋግጥ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ሌባው ባይ​ገኝ ባለ​ቤቱ ወደ ፈጣሪ ፊት ይቅ​ረብ፤ ባል​ን​ጀ​ራው አደራ በአ​ስ​ቀ​መ​ጠ​በት ገን​ዘ​ብም ላይ እን​ዳ​ል​ተ​ተ​ነ​ኰ​ለና ክፉ እን​ዳ​ላ​ሰበ ይማል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ሌባውም ባይገኝ ባለቤቱ ወደ ፈራጆች ይቅረብ፥ እጁንም በባልንጀራው ከብት ላይ እንዳልዘረጋ ይማል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፀአት 22:8
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“አምላክህ ጌታ በሚሰጥህ ከተሞች ሁሉ ለየነገዶችህ ዳኞችንና አለቆችን ሹም፤ እነርሱም ሕዝቡን በቅን ፍርድ ይዳኙ።


ከሙላትህና ከጭማቂህ ለማቅረብ አትዘግይ፤ የልጆችህንም በኩር ትሰጠኛለህ።


ጌታው ወደ እግዚአብሔር ያቅርበው፥ ወደ በሩ ወይም ወደ መቃኑ አቅርቦ ጆሮውን በወስፌ ይብሳው፤ ለዘለዓለምም ያገልግለው።


የአሳፍ መዝሙር። እግዚአብሔር በመለኮታዊ ጉባኤ ቆመ፥ በአማልክትም መካከል ይፈርዳል።


ከእነዚህም ውስጥ የጌታን ቤት ሥራ የሚሠሩት ሀያ አራት ሺህ ነበሩ። ስድስቱ ሺህም አለቆችና ፈራጆች ነበሩ።


አንድ ሰው ለባልንጀራው አህያ ወይም በሬ ወይም በግ ወይም ሌላ እንስሳ እንዲጠብቅለት በአደራ ቢሰጥ፥ ማንም ሳያይ ቢሞት ወይም ቢጎዳ ወይም ቢማረክ፥


“አንድ ሰው ባልንጀራውን ቢበድል፥ አለመበደሉን በመሐላ እንዲያረጋግጥ ሲጠየቅ፥ እርሱም መጥቶ በዚህ ቤት በሚገኘው መሠዊያ ፊት መሐላ ቢያደርግ፥


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች