Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፀአት 22:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ሌባው ግን ባይገኝ፥ እጁን በባልንጀራው ንብረት ላይ እንዳልዘረጋ እንዲታወቅ ባለቤቱ ወደ እግዚአብሔር ፊት ይቅረብ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 “አንድ ሰው ብሩ ወይም ንብረቱ ያለ ሥጋት ይጠበቅለት ዘንድ ለጎረቤቱ ሰጥቶ ሳለ ቢሰርቅበትና፣ ሌባው ቢያዝ ዕጥፍ ይክፈል፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 “አንድ ሰው የሌላውን ሰው ገንዘብ ወይም የከበረ ዕቃ በዐደራ ለመጠበቅ ተስማምቶ ከቤቱ ተሰርቆበት ሌባው ቢገኝ እጥፍ አድርጎ ይክፈል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 “ሰው በባ​ል​ን​ጀ​ራው ዘንድ ብር ወይም ሌላ ዕቃ እን​ዲ​ጠ​ብ​ቅ​ለት አደራ ቢያ​ኖር ከቤ​ቱም ቢሰ​ረቅ፥ ሌባው ቢገኝ እጥፍ ይክ​ፈል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ሰው በባልንጀራው ዘንድ ብር ወይም ሌላ ነገር እንዲጠብቅለት አደራ ቢያኖር ከቤቱም ቢሰረቅ፥ ሌባው ቢገኝ ስለ አንድ ሁለት ይክፈል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፀአት 22:7
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አንድ ሰው በእርሻ ወይም በወይን ስፍራ ከብቱን ቢያሰማራ፥ የሌላውንም ሰው እርሻ ቢያስበላ፥ ከተመረጠ እርሻውና መልካም ከሆንው ወይኑ ይካስ።


ወይም ሌቦች ወይም ስግብግቦች ወይም ሰካራሞች ወይም ተሳዳቢዎች ወይም ነጣቂዎች የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም።


ይህንንም የተናገረው ለድሆች አዝኖላቸው ሳይሆን ሌባ ስለ ነበረ ነው፤ የገንዘብ ከረጢትም ይዞ በውስጡ ከሚገባው ይወስድ ስለ ነበረ ነው።


“ሌባ በተያዘ ጊዜ እንደሚያፍር እንዲሁ የእስራኤል ቤት፥ እነርሱና ንጉሦቻቸውም አለቆቻቸውም ካህናቶቻቸውም ነብዮቻቸውም ያፍራሉ።


አንድ ሰው ብር ወይም ሌላ ነገር እንዲጠብቅለት ለባልንጀራው በአደራ ቢሰጥ፥ ከቤቱም ቢሰረቅና ሌባው ቢገኝ እጥፍ ይክፈል።


ጌታም ሙሴን እንዲህ ሲል ተናገረው፦


“ማናቸውም ሰው ኃጢአትን ቢሠራ፥ በጌታም ላይ ፈጽሞ እምነትን ቢያጎድል፥ በአደራ ከእርሱ ዘንድ የተቀመጠን ነገር ወይም ብድር ወስዶ ባልንጀራውን ቢክድ፥ ወይም ቢቀማ፥ ወይም በባልንጀራው ላይ ግፍ ቢሠራ፥


“በባልንጀራህ ግፍ አታድርግ፥ አትቀማውም። ተቀጥሮ የሚያገለግለውን ሰው ደመወዙን እስከ ነገ ድረስ በአንተ ዘንድ አታቆይበት።


ወይም በሐሰት የማለበትን ምንም ዓይነት ነገር ይመልስ፤ እርሱም የበደሉን መሥዋዕት በሚያቀርብበት ቀን በሙሉ የወሰደውን ነገር ይመልስ፥ በእርሱም ላይ አምስት እጅ ጨምሮበት ለባለቤቱ ይስጠው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች