ዘፀአት 21:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)22 ሰዎች ሲጣሉ፥ ያረገዘችን ሴት ቢመቱ ቢያስወርዳት ነገር ግን እርስ ባትጎዳ፥ የሴቲቱ ባል የጣለበትን ያህል ካሳ ይክፈል፤ ይህም በዳኞቹ ይሰጥ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም22 “በጥል ላይ ያሉ ሰዎች ነፍሰ ጡር ሴት ቢመቱና እርሷም ያለጊዜዋ ብትወልድ፣ ጕዳቱም ለክፉ የማይሰጥ ቢሆን፣ ጕዳት ያደረሰባት ሰው የሴትየዋ ባል የጠየቀውንና ፈራጆቹ የፈቀዱትን ካሣ ሁሉ መክፈል አለበት። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም22 “ሁለት ሰዎች ሲጣሉ አንዲት ነፍሰ ጡር መተው ቢያስወርዳትና ሌላ ምንም ጒዳት ሳይደርስባት ቢቀር፥ ያ ጒዳት ያደረሰባት ሰው የሴቲቱ ባል የሚጠይቀውን ያኽል ካሣ ይክፈል፤ ይህም የሚከፍለው ካሣ መጠን በዳኞች የጸደቀ ይሁን። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)22 “ሁለት ሰዎች እርስ በርሳቸው ቢጣሉ፥ ያረገዘችንም ሴት ቢያቈስሉ ተሥዕሎተ መልክእ ያልተፈጸመለት ፅንስም ቢያስወርዳት፥ የሴቲቱ ባል የጣለበትን ያህል ካሳ ይክፈል፤ ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)22 ሁለት ሰዎች ቢጣሉ፥ ያረገዘችንም ሴት ልጁን እስክትጨነግፍ ቢገፉአት ባትጎዳ ግን፥ የሴቲቱ ባል የጫነበትን ያህል ካሳ ይስጥ፤ ፈራጆቹም እንደ ፈረዱበት ይክፈል። ምዕራፉን ተመልከት |