Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፀአት 21:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 አንድ ሰው ወንድ ባርያውን ወይም ሴት ባርያውን በበትር ቢመታ፥ በእጁም ቢሞትበት፥ ያው ቅጣት ይቀጣ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 “አንድ ሰው ወንድ ወይም ሴት ባሪያውን በዱላ ቢመታና ባሪያውም በዚህ የተነሣ ቢሞት መቀጣት አለበት፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 “አንድ ሰው ወንድም ሆነ ሴት ባሪያውን በበትር ቢመታና ወዲያው ቢሞትበት መቀጣት ይገባዋል፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 “ሰውም ወንድ ባሪ​ያ​ውን ወይም ሴት ባሪ​ያ​ውን በበ​ትር ቢመታ፥ በእጁ ቢሞ​ት​በ​ትም፥ ፈጽሞ ይቀጣ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ሰውም ወንድ ባሪያውን ወይም ሴት ባሪያውን በበትር ቢመታ፥ ቢሞትበትም፥ ፈጽሞ ይቀጣ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፀአት 21:20
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ለመልካም ነገር ለአንተ የእግዚአብሔር አገልጋይ ነውና። ክፉ ብታደርግ ግን ፍራ፤ በከንቱ ሰይፍ አይታጠቅምና፤ ቁጣውን ለማሳየት ክፉ አድራጊውን የሚበቀል የእግዚአብሔር አገልጋይ ነውና።


አገልጋይ በቃል ብቻ አይገሠጽም፥ ቢያስተውል እንኳ አይመልስምና።


ዓይንህም አትራራለት፥ ሕይወት በሕይወት፥ ዐይን በዓይን፥ ጥርስ በጥርስ፥ እጅ በእጅ፥ እግር በእግር፥ ይመለስ።”


ደም ተበቃዩ ራሱ ነፍሰ ገዳዩን ይግደል፤ ባገኛው ጊዜ ይግደለው።


ሰው የተፈጠረው በእግዚአብሔር አምሳያ ስለ ሆነ፥ ሰውን የሚገድል ሁሉ በሰው እጅ ይሞታል።


“ከሆነ ቃየልን ሰባት እጥፍ የበቀል ቅጣት፥ ላሜሕን ግን ሰባ ጊዜ ሰባት።”


እግዚአብሔርም ለእርሱ፥ “እንዲህስ አይሆንም! ማንም ቃየንን የሚገድል፥ ሰባት እጥፍ የበቀል ቅጣት ይደርስበታል” አለው። ጌታም ቃየንን ያገኘው ሁሉ እንዳይገድለው ምልክት አደረገለት።


ተነሥቶም በምርኩዝ ወደ ውጭ ቢወጣ፥ ሥራ ስላስፈታው ገንዘብ ከመክፈልና፥ እስኪፈወስም ድረስ ከማሳከም በቀር የመታው ሰው ከወንጀል ነጻ ነው።


ነገር ግን የተመታው አንድ ወይም ሁለት ቀን ቢቆይ ገንዘቡ ነውና አይቀጣ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች