ዘፀአት 20:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)17 “የባልንጀራህን ቤት አትመኝ፤ የባልንጀራህን ሚስት፥ ወንድ ሠራተኛውን፥ ሴት ሠራተኛውን፥ በሬውን፥ አህያውን፥ የባልንጀራህ የሆነውን ሁሉ ማናቸውንም አትመኝ።” ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም17 የባልንጀራህን ቤት አትመኝ፤ የባልንጀራህን ሚስት ወይም የርሱን ወንድ አገልጋይ ሆነ ሴት አገልጋይ፣ በሬውንም ሆነ አህያውን ወይም የርሱ የሆነውን ማንኛውንም ነገር አትመኝ።” ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም17 “የሌላውን ሰው ቤት አትመኝ፤ ሚስቱን፥ አገልጋዮቹን፥ ከብቱን፥ አህዮቹንም ሆነ ማናቸውንም ንብረቱን ሁሉ አትመኝ።” ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)17 “የባልንጀራህን ሚስት፥ የባልንጀራህን ቤት አትመኝ፤ እርሻውንም፥ ሎሌውንም፥ ገረዱንም፥ በሬውንም፥ አህያውንም፥ ከብቱንም ሁሉ ከባልንጀራህ ገንዘብ ሁሉ ማንኛውንም አትመኝ።” ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)17 የባልንጀራህን ቤት አትመኝ፤ የባልንጀራህን ሚስት ሎሌውንም ገረዱንም በሬውንም አህያውንም ከባልንጀራህ ገንዘብ ሁሉ ማናቸውንም አትመኝ። ምዕራፉን ተመልከት |