ዘፀአት 2:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)7 እኅቱም ለፈርዖን ልጅ፦ “ሕፃኑን እንድታጠባልሽ ሄጄ የምታጠባ ሴት ከዕብራውያን ሴቶች ልጥራልሽን?” አለቻት፤ ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም7 የሕፃኑ እኅት ለፈርዖን ልጅ፣ “ሕፃኑን እያጠባች የምታሳድግልሽ ከዕብራውያን ሴቶች መካከል ሞግዚት ላምጣልሽን?” አለቻት። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም7 በዚያን ጊዜ የሕፃኑ እኅት የንጉሡን ልጅ “ይህን ሕፃን እያጠባች የምታሳድግልሽ ከዕብራውያን ሴቶች አንዲት ሞግዚት ልጥራልሽን?” ስትል ጠየቀቻት። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)7 የዚያም ሕፃን እኅት ለፈርዖን ልጅ፥ “ሕፃኑን ታጠባልሽ ዘንድ ሄጄ የምታጠባ ሴት ከዕብራውያን ሴቶች ልጥራልሽን?” አለቻት። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)7 እኅቱም ለፈርዖን ልጅ፦ “ሕፃኑን ታጠባልሽ ዘንድ ሄጄ የምታጠባት ሴት ከዕብራውያን ሴቶች ልጥራልሽን?” አለቻት፤ ምዕራፉን ተመልከት |