ዘፀአት 2:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)11 በነዚያም ቀኖች፥ ሙሴ ባደገ ጊዜ ወደ ወንድሞቹ ወጣ፥ የሥራቸውንም መከራ ተመለከተ፤ የግብጽም ሰው ከወንድሞቹ አንድ የሆነውን ዕብራዊ ሰው ሲመታ አየ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም11 ሙሴ ካደገ በኋላ አንድ ቀን ወገኖቹ ወደሚገኙበት ስፍራ ወጣ፤ በዚያም ተገድደው ከባድ ሥራ ሲሠሩ ተመለከተ፤ ዕብራዊ ወገኑንም አንድ ግብጻዊ ሲደበድበው አየ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም11 ሙሴ ባደገ ጊዜ ወገኖቹን ለመጐብኘት ሄደ፤ ከባድ ሥራ መሥራታቸውን ተመለከተ፤ እንዲያውም አንድ ግብጻዊ ከወገኖቹ አንዱ የሆነውን ዕብራዊ ሲደበድብ አየ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)11 ከብዙ ቀን በኋላ እንዲህ ሆነ፤ ሙሴ አደገ፤ ወደ ወንድሞቹም ወጣ፤ መከራቸውንም ተመለከተ፤ የግብፅም ሰው ከወንድሞቹ ከእስራኤል ልጆች አንዱን ዕብራዊ ሰው ሲመታ አየ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)11 በዚያም ወራት እንዲህ ሆነ፤ ሙሴ ጎበዝ በሆነ ጊዜ ወደ ወንድሞቹ ወጣ፤ የሥራቸውንም መከራ ተመለከተ፤ የግብፅም ሰው የወንድሞቹን የዕብራውያንን ሰው ሲመታ አየ። ምዕራፉን ተመልከት |