Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘፀአት 18:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 የሙሴ አማት ይትሮ፥ ከልጆቹና ሚስቱ ጋር በምድረ በዳ ሰፍሮ ወደ ነበረበት ወደ እግዚአብሔር ተራራ ወደ ሙሴ መጣ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 የሙሴ ዐማት ዮቶር ከሙሴ ወንድ ልጆችና ሚስት ጋራ ሆኖ በምድረ በዳ ከእግዚአብሔር ተራራ አጠገብ ወደ ሰፈረበት ወደ ሙሴ መጣ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 የትሮ የሙሴ ዐማት ከሙሴ ሚስትና ከሁለቱ ልጆችዋ ጋር ሆኖ በበረሓ ሙሴ ወደ ሰፈረበት ወደ ተቀደሰው ተራራ መጣ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 የሙሴ አማት ዮቶ​ርም ከል​ጆ​ቹና ከሚ​ስቱ ጋር በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተራራ አጠ​ገብ በም​ድረ በዳ ወደ ሰፈረ ወደ ሙሴ መጣ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 የሙሴ አማት ዮቶርም ከልጆቹና ከሚስቱ ጋር በእግዚአብሔር ተራራ አጠገብ በምድረ በዳ ወደ ሰፈረ ወደ ሙሴ መጣ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፀአት 18:5
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ኤልያስም ተነሥቶ ምግቡን በላ፥ ውሃውንም ጠጣ፤ ከዚያም ምግብ ባገኘው ኃይል እስከ ተቀደሰው የሲና ተራራ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ሙሉ ተጓዘ።


ሙሴንም፦ “እኔ አማትህ ይትሮ፥ ሚስትህና ከእርሷም ጋር ሁለቱ ልጆችዋ ወደ አንተ መጥተናል” አለው።


በሦስተኛውም ቀን ይዘጋጁ፤ በሦስተኛው ቀን ሕዝቡ ሁሉ እያዩ ጌታ በሲና ተራራ ላይ ይወርዳልና።


ከራፊድም ተነሥተው ወደ ሲና ምድረ በዳ መጡ፥ በምድረ በዳም ሰፈሩ፤ በዚያም እስራኤል በተራራው ፊት ሰፈረ።


ጌታ በሲና ተራራ ላይ ወደ ተራራው ራስ ወረደ፤ ጌታ ሙሴን ወደ ተራራው ራስ ጠራው፤ ሙሴም ወጣ።


ሙሴና አገልጋዩ ኢያሱ ተነሡ፤ ሙሴም ወደ እግዚአብሔር ተራራ ወጣ።


ሙሴም የምድያን ካህን የሆነውን የአማቹን የይትሮን በጎች ያሰማራ ነበር፤ በጎቹን ከምድረ በዳው ማዶ ነዳቸው፥ ወደ እግዚአብሔርም ተራራ ወደ ኮሬብ መጣ።


እርሱም፦ “እኔ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤ እኔም እንደ ላክሁህ ምልክትህ ይህ ይሆናል፤ ሕዝቡን ከግብጽ ባወጣህ ጊዜ በዚህ ተራራ ላይ እግዚአብሔርን ታገለግላላችሁ” አለ።


ጌታም አሮንን፦ “ሙሴን ለመገናኘት ወደ ምድረ በዳ ሂድ” አለው፤ ሄዶም በእግዚአብሔር ተራራ ተገናኘው፥ ሳመውም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች