ዘፀአት 16:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)13 እንዲህም ሆነ በመሸ ጊዜ ድርጭቶች መጡ፥ ሰፈሩንም ሸፈኑት ማለዳም በሰፈሩ ዙሪያ ጤዛ ነበር። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም13 በዚያች ምሽት ድርጭቶች መጥተው ሰፈሩን አለበሱት፤ በነጋውም በሰፈሩ ዙሪያ ጤዛ ተኝቶበት ነበር። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም13 በምሽትም ብዙ ድርጭቶች እየበረሩ መጥተው ሰፈሩን ሸፈኑት፤ በማለዳ ደግሞ በሰፈሩ ዙሪያ ጤዛ ነበረ፤ ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)13 እንዲህም ሆነ፤ በመሸ ጊዜ ድርጭቶች መጡ፤ ሰፈሩንም ሸፈኑት፤ በማለዳም በሰፈሩ ዙሪያ ጠል ወድቆ ነበር። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)13 እንዲህም ሆነ በመሸ ጊዜ ድርጭቶች መጡ፥ ሰፈሩንም ከደኑት ማለዳም በሰፈሩ ዙሪያ ጠል ወድቆ ነበር። ምዕራፉን ተመልከት |