Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፀአት 15:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ጌታ ተዋጊ ነው፥ ስሙም ጌታ ነው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 እግዚአብሔር ተዋጊ ነው፤ ስሙም እግዚአብሔር ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 እግዚአብሔር ብርቱ ጦረኛ ነው፤ ስሙም እግዚአብሔር ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጦር​ነ​ትን ያጠ​ፋል፤ ስሙም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 እግዚአብሔር ተዋጊ ነው፤ ስሙም እግዚአብሔር ነው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፀአት 15:3
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ይህ የክብር ንጉሥ ማን ነው? ጌታ ነው፥ ብርቱና ኃያል፥ ጌታ ነው፥ በሰልፍ ኃያል።


ጌታ ስለ እናንተ ይዋጋል፥ እናንተም ዝም ትላላችሁ።”


እኔ ጌታ ነኝ፤ ስሜ ይህ ነው፤ ክብሬን ለሌላ፥ ምስጋናዬንም ለተቀረጹ ምስሎች አልሰጥም።


ይፈሩ ለዘለዓለሙም ይታወኩ፥ ይጐስቁሉ ይጥፉም።


ውበትህ ከሰው ልጆች ይልቅ ያምራል፥ ሞገስ በከንፈሮችህ ፈሰሰ፥ ስለዚህ እግዚአብሔር ለዘለዓለም ባረከህ።


እግዚአብሔርም ደግሞ ሙሴን አለው፦ “ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ትላለህ፦ ‘ጌታ የአባቶቻችሁ አምላክ፥ የአብርሃም አምላክ፥ የይስሐቅ አምላክ፥ የያዕቆብም አምላክ ወደ እናንተ ላከኝ፤’ ይህ ለዘለዓለሙ ስሜ ነው፥ እስከ ልጅ ልጅ ድረስም መታሰቢያዬ ይህ ነው።”


ሙሴም እግዚአብሔርን፦ “እኔ ወደ እስራኤል ልጆች ሄጄ፦ ‘የአባቶቻችሁ አምላክ ወደ እናንተ ላከኝ’ ባልሁ ጊዜ፦ ‘ስሙ ማን ነው?’ ቢሉኝ፥ ምን እላቸዋለሁ?” አለው።


ጌታ እንደ ኃያል ይወጣል እንደ ሰልፈኛም ቅንዓትን ያስነሣል፤ ይጮኻል ድምፁንም ያሰማል በጠላቶቹም ላይ ይበረታል።


“ስሙ ጌታ የሆነ፥ ምድርንም የፈጠረ ጌታ፥ ሊያጸናውም የሠራው ጌታ እንዲህ ይላል፦


እግዚአብሔርም ሙሴን፦ “የምኖር እኔ ነኝ” አለው፤ ስለዚህ ለእስራኤል ልጆች፦ “‘የምኖር’ ወደ እናንተ ላከኝ በላቸው” አለው።


የሰረገሎቹንም ጎማ አሰረ፥ ወደ ጭንቅም አስገባቸው፤ ግብፃውያንም፦ “ጌታ ግብፃውያንን ይዋጋላቸዋልና ከእስራኤል ፊት እንሽሽ” አሉ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች