Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፀአት 15:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 እርሱም፦ “አንተ የጌታ አምላክህን ቃል ብትሰማ፥ በፊቱም ትክክል የሆነውን ብታደርግ፥ ትእዛዙንም ብታደምጥ፥ ሥርዓቱንም ሁሉ ብትጠብቅ፥ በግብፃውያን ላይ ያመጣሁትን በሽታ አላመጣብህም፤ ፈዋሽህ እኔ ጌታ ነኝና” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 እርሱም አለ፤ “የአምላካችሁን እግዚአብሔር ድምፅ በጥንቃቄ ብትሰሙ፣ በፊቱም ትክክል የሆነውን ብትፈጽሙ፣ ትእዛዞቹን ልብ ብትሉና ሥርዐቱንም ሁሉ ብትጠብቁ፣ በግብጻውያን ላይ ያመጣሁባቸውን ማንኛውንም ዐይነት በሽታ በእናንተ ላይ አላመጣም፤ ፈዋሻችሁ እኔ እግዚአብሔር ነኝና።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 እንዲህም አላቸው፤ “በጥሞና ትእዛዞቼን ብታዳምጡና በፊቴ መልካም የሆነውን ነገር በታዛዥነት ብታደርጉ፥ ኅጎቼንም ሁሉ ብትጠበቁ፥ በግብጻውያን ላይ ካመጣሁባቸው በሽታዎች በአንዱ እንኳ አልቀጣችሁም፤ ፈዋሻችሁ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 እር​ሱም፥ “አንተ የአ​ም​ላ​ክ​ህን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል አጥ​ብ​ቀህ ብት​ሰማ፥ በፊ​ቱም መል​ካ​ምን ብታ​ደ​ርግ፥ ትእ​ዛ​ዙ​ንም ብታ​ደ​ምጥ፥ ሥር​ዐ​ቱ​ንም ሁሉ ብት​ጠ​ብቅ፥ በግ​ብ​ፃ​ው​ያን ላይ ያመ​ጣ​ሁ​ትን በሽታ አላ​ደ​ር​ስ​ብ​ህም፤ እኔ ፈዋ​ሽህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝና” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 እርሱም፦ አንተ የአምላክህን የእግዚአብሔርን ቃል አጥብቀህ ብትሰማ፥ በፊቱም የሚበጀውን ብታደርግ፥ ትእዛዙንም ብታደምጥ፥ ሥርዓቱንም ሁሉ ብትጠብቅ፥ በግብፃውያን ላይ ያመጣሁትን በሽታ አላደርስብህም፤ እኔ ፈዋሽህ እግዚአብሔር ነኝና አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፀአት 15:26
42 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ጥፋትሽንም ሁሉ ይቅር የሚል፥ ደዌሽንም ሁሉ የሚፈውስ፥


ጌታም ሕማምን ሁሉ ከአንተ ያርቃል፥ የምታውቀውንም ክፉውን የግብጽ በሽታ ሁሉ በአንተ ላይ አያደርስብህም፥ በሚጠሉህ ሁሉ ላይ ግን ያመጣባቸዋል።


ጌታ አምላካችሁን ታገለግላላችሁ፤ እርሱም እህልህንና ውኃህን ይባርካል፤ በሽታንም ከመካከልህ አርቃለሁ።


ልባቸው የተሰበረባቸውን ይፈውሳል፥ ሕማማቸውንም ይጠግናል።


እነሆ፥ ፈውስንና መድኃኒትን አመጣላታለሁ፥ እፈውሳቸዋለሁም፤ እጅግም የበዛ ሰላምንና እውነትን እገልጥላቸዋለሁ።


እንዲህም ይላሉ፦ “ኑ፥ ወደ ጌታ እንመለስ፤ እርሱ ሰብሮናልና፥ እርሱም ይፈውሰናል፤ እርሱ መትቶናል፥ እርሱም ይጠግነናል።


ባርያዎች እዳትሆኑአቸው ከግብጽ ምድር ያወጣኋችሁ እኔ ጌታ አምላካችሁ ነኝ፤ የባርነታችሁን ቀንበር ሰብሬአለሁ፤ ቀና ብላችሁም እንድትሄዱ አድርጌአችኋለሁ።”


እርሱ ቢያቈስልም ይጠግናልና፥ ቢሰብርም፥ እጆቹ ይፈውሳሉና።


ደግሞም የምትፈራውን የግብጽ በሽታ ሁሉ ያመጣብሃል፤ በአንተም ላይ ይጣበቃሉ።


በአምላክህ በጌታ ፊት መልካምና ትክክል የሆነውን ነገር ስለምታደርግ፥ ለአንተና ከአንተም በኋላ ለሚመጡት ልጆችህ ለዘለዓለም መልካም እንዲሆንላችሁ፥ እኔ የምሰጥህን እነዚህን ደንቦች ሁሉ በጥንቃቄ ፈጽማቸው።”


ይህንንም የማደርገው ሰሎሞን እኔን ትቶ ባዕዳን የሆኑትን ዐስታሮት ተብላ የምትጠራውን የሲዶና አምላክ፥ ኬሞሽ ተብሎ የሚጠራውን የሞዓብ አምላክና ሚልኮም ተብሎ የሚጠራውን የዐሞን አምላክ ስላመለከ ነው፤ ሰሎሞን ለእኔ ታዛዥ አልሆነም፤ እርሱ አባቱ ዳዊት ለእኔ ይታዘዝ እንደ ነበር ሕጎቼንና ትእዛዞቼን ባለመጠበቁ በድሎአል።


መንገዶቹን አይቻለሁ፤ ቢሆንም እፈውሰዋለሁ፤ እመራዋለሁ፤ ለእርሱና ስለ እርሱ ለሚያለቅሱትም መጽናናትን እሰጣለሁ።


ይህም የሚሆነው፥ ዛሬ እኔ የማዝዝህን ትእዛዝ ሁሉ ከጠበቅህ፥ በጌታ በአምላክህ ፊት ትክክል የሆነውን ካደረግህ፥ የጌታ የአምላክህን ቃል ከሰማህ ነው።”


“ሕዝቤን ወደሚመራው ወደ ንጉሥ ሕዝቅያስ ተመልሰህ በመግባት እንዲህ በለው፦ ‘እኔ የቀድሞ አባትህ የዳዊት አምላክ እግዚአብሔር ጸሎትህን ሰምቻለሁ፤ እንባህንም ተመልክቻለሁ፤ እኔ እፈውስሃለሁ፤ ከሦስት ቀንም በኋላ ወደ ቤተ መቅደስ ትወጣለህ፤


በማትድንበት በግብጽ ብጉንጅ፥ በእባጭ፥ በሚመግል ቁስልና በዕከክ ጌታ ያሠቃይሃል።


ሰው ጻድቅ ቢሆን፥ ፍትሕንና ጽድቅን ቢያደርግ፥


በገለዓድ የሚቀባ መድኃኒት የለምን? ወይስ በዚያ ሐኪም የለምን? የወገኔ ሴት ልጅ ፈውስ ስለምን አልሆነም?


ኢዮስያስ የቀድሞ አባቱን የዳዊትን መልካም ምሳሌነት በመከተልና ለእግዚአብሔር ሕግ ፍጹም ታዛዥ በመሆን፥ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሥራ ሠራ።


“በሥርዓቶቼ ብትመላለሱ፥ ትእዛዛቴንም ብትጠብቁ ብታደርጉአቸውም፥


አገልጋዬ ዳዊት እንዳደረገው በፍጹም ልብህ ብትታዘዘኝ፥ በሕጎቼና በትእዛዞቼ ጸንተህ ብትኖር፥ በእኔ ፊት ሞገስ ብታገኝ፥ እኔ ዘወትር ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤ በእስራኤል ላይ እንድትነግሥም አደርግሃለሁ፤ ለዳዊት ባደረግሁት ዓይነት ዘሮችህ ከአንተ በኋላ እንደሚነግሡ አረጋግጥልሃለሁ።


“በዚህ መጽሐፍ የተጻፈውን የዚህን ሕግ ቃሎች በጥንቃቄ ባትከተልና አስደናቂና አስፈሪ የሆነውን የጌታ እግዚአብሔርን ስም ባታከብር፥


እንዲህም ሆነ እኩለ ሌሊት ላይ ጌታ በግብጽ ምድር ያለውን በኩር ሁሉ፥ በዙፋን ከተቀመጠው ከፈርዖን በኩር ጀምሮ በእስር ቤት እስካሉት እስከ እስረኞች በኩር ድረስ፥ የከብቶችንም በኩር ሁሉ መታ።


አሁንም ቃሌን በእውነት ብትሰሙ ኪዳኔንም ብትጠብቁ፥ ምድር ሁሉ የእኔ ናትና ከአሕዛብ ሁሉ የተመረጠ ርስት ትሆኑልኛላችሁ፤


የካህናት መንግስት፥ የተቀደሰም ሕዝብ ትሆኑልኛላችሁ። ለእስራኤል ልጆች የምትነግራቸው ቃል ይህ ነው።”


“ከግብጽ ምድር ከባርነት ቤት ያወጣሁህ ጌታ አምላክህ እኔ ነኝ።


በጌታ ፊት ትክክል የሆነውን ነገር ስለምታደርግ፥ ለአንተም ሆነ ከአንተ በኋላ ለሚመጡት ልጆችህ መልካም እንዲሆንላቸው አትብላው።


“እኔ ራሴ እርሱ እንደሆንሁ እዩ፤ ከእኔም በቀር ሌላ አምላክ የለም፤ እኔ እገድላለሁ፤ በሕይወትም አኖራለሁ፤ እኔ አቆስላለሁ፤ እፈውሳለሁም፤ ከእጄም የሚያስጥል ማንም የለም።


እርሱም ወደ ምንጩ ሄዶ ጨውን በውሃው ውስጥ በመጨመር፥ “እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው ‘እኔ ይህን ውሃ በመፈወስ ንጹሕ እንዲሆን አደርጋለሁ፤ ከዚህም በኋላ ዳግመኛ የሞትና የምርት አልባነት ምክንያት አይሆንም’” ሲል ተናገረ፤


ነገር ግን፦ “ድምፄን ስሙ፥ እኔም አምላክ እሆናችኋለሁ እናንተም ሕዝብ ትሆኑኛላችሁ፤ መልካምም እንዲሆንላችሁ ባዘዝኋችሁ መንገድ ሁሉ ሂዱ” ብዬ በዚህ ነገር አዘዝኋቸው።


አባቶቻችሁን ከግብጽ ምድር ካወጣሁበት ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ፥ በማለዳ በመነሳት ደጋግሜ እያስጠነቀቅሁ፦ ድምፄን ስሙ በማለት አስጠንቅቄአቸው ነበር።


“ ‘እኔን ፈጽሞ ብትሰሙ፥ ይላል ጌታ፥ በሰንበትም ቀን በዚህች ከተማ በሮች ሸክም ባታስገቡ፥ የሰንበትንም ቀን ብትቀድሱ ሥራንም ሁሉ ባትሠሩበት፥


‘ማንም የማይሻት ጽዮን!’ ‘የተጣለች’ ብለው ጠርተውሻልና እኔ ጤናሽን እመልስልሻለሁ ቁስልሽንም እፈውሳለሁ፥ ይላል ጌታ።


ሙሴም እንዲህ ብሎ ወደ ጌታ ጮኸ፦ “አቤቱ፥ እባክህ፥ ፈውሳት።”


ሙሴም እስራኤልን ሁሉ ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ “እስራኤል ሆይ፥ እንድትማሩአት በማድረግም እንድትጠብቁአት ዛሬ በጆሮአችሁ የምናገራትን ሕግና ሥርዓት ስሙ።


ሕዝቤ ሆይ፥ ስማኝ እነግርሃለሁም፥ እስራኤል ሆይ፥ ምነው በሰማኸኝ!


ጆሮአችሁን አዘንብሉ ወደ እኔም ቅረቡ፤ ሰውነታችሁ በሕይወት እንድትኖር ስሙኝ፥ የታመነችይቱን የዳዊትን ምሕረት፥ የዘለዓለምን ቃል ኪዳን ከእናንተ ጋር አደርጋለሁ።


እኔም ኤፍሬምን ክንዱን ይዤ መራመድን አስተማርሁት፤ እኔም እፈውሳቸው እንደ ነበርሁ አላወቁም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች