Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፀአት 15:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ጌታ ኃይሌና መዝሙሬ ነው፥ መድኃኒቴም ሆነልኝ፤ ይህ አምላኬ ነው አመሰግነዋለሁም፥ የአባቴ አምላክ ከፍ ከፍ አደርገዋለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 “እግዚአብሔር ብርታቴና ዝማሬዬ ነው፤ ድነቴም ሆነልኝ፤ እርሱ አምላኬ ነው፤ አመሰግነዋለሁ፤ የአባቴ አምላክ ነው፤ እኔም ከፍ ከፍ አደርገዋለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 እግዚአብሔር በመዝሙር የማመሰግነው መከላከያ ኀይሌ ነው፤ ከጠላት እጅ ያዳነኝ ታዳጊዬም እርሱ ነው፤ እርሱ አምላኬ ስለ ሆነ አመሰግነዋለሁ፤ የአባቴም አምላክ ስለ ሆነ፥ ስለ ገናናነቱ እዘምራለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 እኔን ለማ​ዳን ረዳ​ትና ሰዋሪ ሆነኝ፤ ይህ አም​ላኬ ነው፤ አመ​ሰ​ግ​ነ​ው​ማ​ለሁ፤ የአ​ባቴ አም​ላክ ነው፤ ከፍ ከፍም አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 ጉልበቴ ዝማሬዬም እግዚአብሔር ነው፤ መድኃኒቴም ሆነልኝ፤ ይህ አምላኬ ነው አመሰግነውማለሁ፤ የአባቴ አምላክ ነው ከፍ ከፍም አደርገዋለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፀአት 15:2
64 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እነሆ፤ ጌታ መዳኛዬ ነው፤ እታመናለሁ፤ ደግሞም አልፈራም፤ ጌታ እግዚአብሔር ብርታቴና ዝማሬዬ ነው፤ የመዳኔ ምክንያትም ሆኖአል።”


ኃይሌም ዝማሬዬም ጌታ ነው፥ እርሱም መድኃኒት ሆነልኝ።


የባዕድ ልጆች ጠወለጉ፥ በመንቀጥቀጥም ከምሽጋቸው ወጥተው ወደ እኔ መጡ።


እኔ ግን ለኃይልህ እቀኛለሁ፥ በምሕረትህም ማልዶ ደስ ይለኛል፥ በመከራዬ ቀን መጠጊያዬና አምባዬ ሆነኸኛልና።


አቤቱ ጌታ፥ አንተ አምላኬ ነህ፤ አስቀድሞ የታሰበውን፤ ድንቅ ነገር በታማኝነትና በእውነት አድርገሃልና ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ ስምህንም አመሰግናሁ።


ጌታንም፦ አንተ አምላኬ ነህ፥ የልመናዬን ቃል፥ አቤቱ፥ አድምጥ አልሁት።


ጌታ አምላካችንን ከፍ ከፍ አድርጉት፥ በቅዱስ ተራራውም ስገዱ፥ ጌታ እግዚአብሔር ቅዱስ ነውና።


“ሁሉን የምትገዛ ጌታ አምላክ ሆይ! ሥራህ ታላቅና ድንቅ ነው፤ የአሕዛብ ንጉሥ ሆይ! መንገድህ ትክክልና እውነተኛ ነው፤ ጌታ ሆይ! የማይፈራህና ስምህን የማያከብር ማን ነው? አንተ ብቻ ቅዱስ ነህና፤ የጽድቅም ሥራህ ስለ ተገለጠ አሕዛብ ሁሉ ይመጣሉ፤ በፊትህም ይሰግዳሉ፤” እያሉ የእግዚአብሔርን ባርያ የሙሴን ቅኔና የበጉን ቅኔ ይዘምራሉ።


መላስ ሁሉ ለእግዚአብሔር አብ ክብር እንዲሆን ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንደሆነ እንዲመሰክሩ ነው።


አንተ አምላኬ ነህ አመሰግንሃለሁ። አንተ አምላኬ ነህ፥ ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ፥ ሰምተኸኛልና፥ መድኃኒትም ሆነኸኛልና አመሰግንሃለሁ።


ጌታ አምላካችንን ከፍ ከፍ አድርጉት፥ ቅዱስ ነውና ወደ እግሩ መርገጫ ስገዱ።


ነፍሴ በጌታ ትከብራለች፥ ገሮችም ሰምተው ደስ ይላቸዋል።


ዐይኖችህ ያዩትን እነዚህን ታላላቅና የሚያስፈሩ ነገሮችን ያደረገልህ እርሱ ክብርህ ነው፥ እርሱ አምላክህ ነው።


እርሱም፦ “እኔ የአባትህ አምላክ፥ የአብርሃም አምላክ፥ የይስሐቅ አምላክ፥ የያዕቆብም አምላክ ነኝ” አለው። ሙሴም ወደ እግዚአብሔር ማየት ፈርቶ ፊቱን ሸፈነ።


ይህ እግዚአብሔር የሰዎችን በደል ሳይቆጥርባቸው በክርስቶስ ዓለምን ከራሱ ጋር አስታርቋል፤ በእኛም የማስታረቅ ቃል አኑሯል።


መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና።”


የዳዊት የምስጋና መዝሙር። አምላኬ ንጉሤ ሆይ፥ ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ፥ ስምህንም ለዘለዓለም ዓለምም እባርካለሁ።


ጌታ ሕያው ነው! ዐለቴ የተባረከ ይሁን፤ የመዳኔ ዓለት አምላኬ ከፍ ከፍ ይበል።


ሙሴም ሕዝቡን እንዲህ አላቸው፦ “አትፍሩ፥ ቁሙ፥ ዛሬ ለእናንተ የሚያደርጋትን የጌታን ማዳን እዩ ዛሬ የምታዩአቸውን ግብፃውያንን ለዘለዓለም አታዩአቸውምና።


ፈርዖንንም ትለዋለህ፦ ‘ጌታ እንዲህ ይላል፦ እስራኤል የበኩር ልጄ ነው፤


በእርሱም እናንተ ደግሞ ለእግዚአብሔር መኖሪያ ለመሆን በመንፈስ አብራችሁ ትሠራላችሁ።


እርሱም፦ “የያዕቆብን ነገዶች እንድታስነሣ ከእስራኤልም የተረፉትን እንድትመልስ አገልጋዬ እንድትሆን እጅግ ቀላል ነገር ነውና ማዳኔ እስከ ምድር ዳር እንዲደርስ ለአሕዛብ ብርሃን አድርጌ ሰጥቼሃለሁ ይላል።


ለመዘምራን አለቃ፥ የዳዊት መዝሙር። አምላክ ሆይ፥ ምስጋናዬን ዝም አትበል፥


ሳይቀባ፥ የዳዊት መዝሙር። ጌታ ብርሃኔና መድኃኒቴ ነው፥ የሚያስፈራኝ ማን ነው? ጌታ የሕይወቴ ከለላዋ ነው፥ የሚያስደነግጠኝ ማን ነው?


ከዚህ በኋላ ደመናው የመገናኛውን ድንኳን ሸፈነ፥ የጌታም ክብር ማደሪያውን ሞላ።


ከዚህ በኋላ በሰማይ የብዙ ሕዝብ ታላቅ ድምፅን የመሰለ ድምፅ ሰማሁ፦ “ሃሌ ሉያ! ማዳንና ክብር ኃይልም የአምላካችን ነው፤”


ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን ነገር ማድረግ እችላለሁ።


ሰዎች ሁሉ አብን እንደሚያከብሩት ወልድን ያከብሩት ዘንድ ነው፤ወልድን የማያከብር የላከውን አብን አያከብርም።


እናንተስ ለማታውቁት ትሰግዳላችሁ፤ እኛ ለምናውቀው እንሰግዳለን፥ መዳን ከአይሁድ ነውና።


ዐይኖቼ ማዳንህን አይተዋልና፤


እንዲሁም በኀጢአታቸው ስርየት የመዳንን እውቀት ለሕዝቡ ትሰጣለህ፤


አንድ ሦስተኛውን ክፍል ወደ እሳት አስገባለሁ፤ ብርም እንደሚነጥር አነጥራቸዋለሁ፤ ወርቅም እንደሚፈተን እፈትናቸዋለሁ፤ እነርሱም ስሜን ይጠራሉ፥ እኔም እሰማቸዋለሁ፤ እኔም፦ “ይህ ሕዝቤ ነው” እላለሁ፥ እርሱም፦ “ጌታ አምላኬ ነው” ይላል።


እነርሱም ሕዝብ ይሆኑኛል እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ።


ከእነዚያ ወራት በኋላ ከእስራኤል ቤት ጋር የማደርገው ቃል ኪዳን ይህ ነውና፥ ይላል ጌታ፤ ሕጌን በልቡናቸው አኖራለሁ፥ በልባቸውም እጽፈዋለሁ፤ እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑኛል።


በእውነት ኮረብቶች ሐሰት ናቸው፥ በተራሮችም ላይ ሁከት ነው፤ በእውነት የእስራኤል መዳን በአምላካችን በጌታ ነው።”


ጌታ እንዲህ ይላል፦ ሰማይ ዙፋኔ ነው፥ ምድርም የእግሬ መረገጫ ናት፤ የምትሠሩልኝ ቤት ምን ዓይነት ነው? የማርፍበትስ ስፍራ ምንድነው?


ጌታ ግን እስራኤልን በዘላለማዊ መድኃኒት ያድነዋል፥ እናንተም ለዘለዓለም አታፍሩምና አትዋረዱም።


ለጌታ ስፍራ፥ ለያዕቆብ ኀያል ማደሪያ እስካገኝ ድረስ ብሎ።


በየዕለቱ የሚንከባከበን ጌታ የተመሰገነ ይሁን፥ እግዚአብሔር ያድነናል።


ለቤቱ መመረቅ ምስጋና፥ የዳዊት መዝሙር።


ጌታ ለሕዝቡ ኃይላቸው ነው፥ ለቀባውም የመድኃኒቱ መታመኛ ነው።


አንተ ግን ከሆድ አውጥተኸኛልና፥ በእናቴ ጡት ሳለሁም በአንተ ታመንሁ።


አምላኬ፥ በቀን ወደ አንተ እጠራለሁ፥ አልመለስህልኝም፥ በሌሊትም እንኳ ዕረፍት የለኝም።


“በውኑ እግዚአብሔር በምድር ላይ ይኖራልን? እነሆ ሰማያት፥ ከሰማያትም በላይ ያለው ሰማይ ሊይዝህ አይችልም፤ እኔ የሠራሁት ይህ ቤተ መቅደስማ ምንኛ ያንስ!


እኔም ለዘለዓለም የምትኖርበት ማደሪያ ቤት በእውነት ሠራሁልህ አለ። እኔም አሁን ግርማ ሞገስ ያለው ማደሪያ ቤት ሠርቼልሀለሁ፤ ለዘለዓለም ማደሪያህ ቦታም ይሆናል።”


ለንጉሡ ታላቅ ድል ይሰጠዋል፤ ለቀባው ለዳዊትና ለዘሩ፥ የማይለወጥ ፍቅሩን ያሳያል፥ ይህንንም ለዘለዓለም ያደርጋል።”


“ሂድና አገልጋዬን ዳዊትን፥ ጌታ እንዲህ ይላል፤ ‘እኔ የምኖርበትን ቤተ መቅደስ የምትሠራልኝ አንተ ነህን?’


ቃል ኪዳኔንም በእኔና በአንተ መካከል ከአንተም በኋላ ከዘርህ ጋር በትውልዳቸው ለዘለዓለም ኪዳን አቆማለሁ፥ ለአንተና ከአንተ በኋላ ለዘርህ አምላክ እሆን ዘንድ።


በእርሱ የመለኮት ሙላት ሁሉ በአካል ተገልጦ ይኖራልና፤


ጌታ ሆይ፥ መድኃኒትህን እጠብቃለሁ።


ከዱሮ ጀምሮ የታወቀ ያ የቂሶን ወንዝ፥ የቂሶን ወንዝ ጠርጎ ወሰዳቸው። ነፍሴ ሆይ፥ በኃይል እርገጪ።


በብርታትዋ ልባችሁን አኑሩ፥ ቅጥሮችዋን መርምሩ፥ ለሚመጣው ትውልድ ትነግሩ ዘንድ።


ሕዝብህን ለመታደግ፥ የቀባኸውንም ለማዳን ወጣህ፤ የኃጢአተኛውን ቤት ራስ ቀጠቀጥህ፥ ከመሠረቱ እስከ አንገቱ ድረስ አራቆትህ።


ለእኔ ሕዝብ አድርጌ እቀበላችኋለሁ፥ አምላክም እሆናችኋለሁ፤ እኔም ከግብጽ ጭቆና ያወጣኋችሁ ጌታ አምላካችሁ እንደሆንሁ ታውቃላችሁ።


ሕዝብህን እስራኤልን ለዘለዓለም ያንተው የራስህ ሕዝብ አድርገህ አጽንተኸዋል፤ ጌታ ሆይ፤ አንተም አምላክ ሆነኸዋል።


አምላኬ የምደገፍበት፥ ዐለቴ፥ ጋሻዬና የመዳኔ ቀንድ ነው። እርሱም ጠንካራ ምሽጌ፥ መጠጊያና አዳኜ ነው፤ አንተ ከጨካኞች ታድነኛለህ።


እርሱ ጌታ አምላካችን ነው፤ ፍርዱ በምድር ሁሉ ነው።


ሰምተኸኛልና፥ መድኃኒትም ሆነኸኛልና አመሰግንሃለሁ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች