Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፀአት 14:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 ሙሴም እጁን በባሕሩ ላይ ዘረጋ፥ ባሕሩም ማለዳ ወደ መፍሰሱ ወደ ቀድሞ ሁኔታው ተመለሰ፤ ግብፃውያንም ከእርሱ ሸሹ፥ ጌታም ግብፃውያንን በባሕሩ መካከል ጣላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 ሙሴም እጁን በባሕሩ ላይ ዘረጋ፤ ንጋት ላይም ባሕሩ ወደ ቀድሞ ቦታው ተመለሰ። ግብጻውያን ከውሃው ሸሹ፤ እግዚአብሔርም ግብጻውያንን በባሕሩ ውስጥ ጣላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 ስለዚህ ሙሴ እጁን ወደ ባሕሩ ዘረጋ፤ ጎሕ ሲቀድ ውሃው ወደ ቀድሞ ቦታው ተመለሰ፤ ግብጻውያንም ከውሃው ሸሽተው ለመውጣት ሞከሩ፤ እግዚአብሔር ግን በባሕር ውስጥ ጣላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 ሙሴም እጁን በባ​ሕሩ ላይ ዘረጋ፤ ባሕ​ሩም ማለዳ ወደ መፍ​ሰሱ ተመ​ለሰ፤ ግብ​ፃ​ው​ያ​ንም ከእ​ርሱ ሸሹ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ግብ​ፃ​ው​ያ​ንን በባ​ሕሩ መካ​ከል ጣላ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 ሙሴም እጁን በባሕሩ ላይ ዘረጋ፤ ባሕሩም ማለዳ ወደ መፍሰሱ ተመለሰ፤ ግብፃውያንም ከእርሱ ሸሹ፤ እግዚአብሔርም ግብፃውያንን በባሕሩ መካከል ጣላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፀአት 14:27
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የጌታንም የቃል ኪዳኑን ታቦት የተሸከሙ ካህናት ከዮርዳኖስ መካከል በወጡ ጊዜ፥ የካህናቱም እግር ጫማ ደረቅ መሬት መርገጥ በጀመረ ጊዜ፥ የዮርዳኖስ ውኃ ወደ ስፍራው ተመለሰ፥ ቀድሞም እንደ ነበረ ከአፉ እስከ ደፉ ሞልቶ በዳርቻው ሁሉ ፈሰሰ።


በተስፋም መራቸው አልፈሩምም፥ ጠላቶቻቸውንም ባሕር ደፈናቸው።


በደረቅ ምድር እንደሚያልፉ የኤርትራን ባሕር በእምነት ተሻገሩ፤ የግብጽ ሰዎች ግን ሲሞክሩ ሰመጡ።


በግብፃውያን ሠራዊት፥ በፈረሶቻቸውና በሠረገሎቻቸው ላይ፥ እናንተን ባሳደዱአችሁ ጊዜ በቀይ ባሕር ውሃ እንዴት እንዳሰጠማቸውና ጌታ ፈጽሞ እንዴት እንዳጠፋቸው አስታውሱ፤


በፊታቸውም ባሕሩን ከፈልህ፥ በባሕሩ መካከል በደረቅ ምድር ተሻገሩ፤ አሳዳጆቻቸውን ግን በኃይለኛ ውኃ እንደሚጣል ድንጋይ ወደ ጥልቁ ጣልካቸው።


ያሳደዱአቸውንም ውኃ ዋጣቸው፥ ከእነርሱም አንድ አልቀረም።


ፈርዖንንና ሠራዊቱን በኤርትራ ባሕር የጣለውን፥ ፍቅሩ ለዘለዓለም ነውና፥


የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ምድያምን በሔሬብ ዐለት አካባቢ እንደ መታ፤ በጅራፍ ይገርፋቸዋል፤ በግብጽ እንዳደረገውም ሁሉ፤ በትሩን በውሆች ላይ ያነሣል።


ወደ ጌታም በጮኹ ጊዜ በእናንተና በግብፃውያን መካከል ጨለማ አደረገ፥ ባሕሩንም መለሰባቸው፥ አሰጠማቸውም፤ ዐይኖቻችሁም በግብጽ ያደረግሁትን አዩ፤ በምድረ በዳም ብዙ ጊዜ ተቀመጣችሁ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች