ዘፀአት 13:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)16 ጌታ በብርቱ እጅ ከግብጽ አውጥቶናልና በእጅህ እንደ ምልክት፥ በዐይኖችህም መካከል እንደ ተንጠለጠለ ነገር ይሁንልህ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም16 እግዚአብሔር በኀያል ክንዱ እኛን ከግብጽ ያወጣን ስለ ሆነ ይህ ሥርዐት በእጅህም ሆነ በግንባርህ ላይ እንደ ምልክት ይሆናል።” ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም16 ይህም ሥርዓት በእጃችን እንደ ታሰረና በግንባራችን ላይ እንደሚገኝ ምልክት ማስታወሻ ይሆናል፤ እግዚአብሔር በታላቅ ኀይሉ ከግብጽ ምድር እንዳወጣንም ያስታውሰናል።’ ” ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)16 እግዚአብሔርም በብርቱ እጅ ከግብፅ አውጥቶሃልና በእጅህ እንደ ምልክት ፥ ከዐይኖችህም እንደማይርቅ ነገር ይሁንልህ።” ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)16 እግዚአብሔርም በብርቱ እጅ ከግብፅ አውጥቶናልና በእጅህ እንደ ምልክት፥ በዓይኖችህም መካከል እንደ ተንጠለጠለ ነገር ይሁንልህ።’” ምዕራፉን ተመልከት |