Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፀአት 12:42 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

42 ከግብጽ ምድር ስላወጣቸው ለጌታ የተጠበቀች ሌሊት ናት፤ ይህች ሌሊት በእስራኤል ልጆች ሁሉ ዘንድ በትውልዳቸው ሁሉ ለጌታ የተጠበቀች ናት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

42 እግዚአብሔር በዚያች ሌሊት እነርሱን ከግብጽ ለማውጣት ዘብ የቆመበት በመሆኑ፣ ለሚቀጥሉት ትውልዶች ሁሉ እግዚአብሔርን ያከብሩ ዘንድ፣ በዚያች ሌሊት እስራኤላውያን ሁሉ ዘብ መቆም ይኖርባቸዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

42 እግዚአብሔር ሕዝቡን እየጠበቀ ከግብጽ ምድር ባወጣቸው ዕለት ጊዜው ሌሊት ነበር፤ ያም ሌሊት እስራኤላውያን በመጠባበቅ ተግተው የሚያድሩበት ለሚመጣው ትውልድ ሁሉ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ሌሊት ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

42 ይህች ሌሊት ከግ​ብፅ ምድር ስላ​ወ​ጣ​ቸው ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ጠ​በ​ቀች ናት፤ ይህች ሌሊት በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሁሉ ዘንድ እስከ ልጅ ልጃ​ቸው ድረስ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ጠ​በ​ቀች ናት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

42 ይህች ሌሊት ከግብፅ ምድር ስላወጣቸው ለእግዚአብሔር የተጠበቀች ናት፤ ይህች ሌሊት በእስራኤል ልጆች ሁሉ ዘንድ እስከ ልጅ ልጃቸው ድረስ ለእግዚአብሔር የተጠበቀች ናት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፀአት 12:42
6 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ይህም ቀን መታሰቢያ ይሁናችሁ፥ በዓል አድርጋችሁ ጠብቁት፥ ለጌታ በዓል ነው፤ ለትውልዳችሁ ለዘለዓለም ሥርዓት አድርጋችሁ ትጠብቁታላችሁ።


በተወሰነለት ጊዜ ከዓመት ወደ ዓመት ይህችን ሥርዓት ጠብቃት።


ሙሴም ሕዝቡን አለ፦ ከባርነት ቤት ከግብጽ የወጣችሁበትን ይህንን ቀን አስቡ፥ ጌታ ከዚህ ቦታ በብርቱ እጅ አውጥቶአችኋልና ስለዚህ የቦካ እንጀራ አትብሉ።


“የቂጣውን በዓል ጠብቀው፤ በአቢብ ወር ከግብጽ ወጥተሃልና በተወሰነው ጊዜ በአቢብ ወር እንዳዘዝሁህ ሰባት ቀን ቂጣ ብላ።


እስራኤልንም ከመካከላቸው ያወጣውን፥ ፍቅሩ ለዘለዓለም ነውና፥


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች