ዘፀአት 11:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)8 እነዚህም አገልጋዮችህ ሁሉ ወደ እኔ ይወርዳሉ፥ ለእኔም ይሰግዳሉ፥ ‘አንተ ውጣ በሥርህ ያለ ሕዝብ ሁሉ ይውጣ’ ይላሉ፤ ከዚያም በኋላ እወጣለሁ።” ሙሴም በጽኑ ቁጣ ከፈርዖን ዘንድ ወጣ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም8 ሹማምትህ በሙሉ ወደ እኔ ይመጣሉ፤ እጅ እየነሡም ‘አንተም ሆንህ የምትመራቸው ሰዎች በሙሉ ውጡልን’ ብለው ይለምኑኛል፤ እኔም ከዚያ በኋላ እሄዳለሁ።” ከዚያም ሙሴ በታላቅ ቍጣ ከፈርዖን ዘንድ ወጣ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም8 ሙሴም “መኳንንትህ ሁሉ ወደ እኔ መጥተው እጅ ይነሡኛል፤ ሕዝቤንም ይዤ እንድወጣ ይለምኑኛል፤ ከዚያም በኋላ እሄዳለሁ” በማለት ንግግሩን አበቃ፤ ይህንንም ከተናገረ በኋላ በታላቅ ቊጣ ከንጉሡ ፊት ወጥቶ ሄደ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)8 እነዚህ አገልጋዮችህ ሁሉ፦ አንተ ውጣ፤ የሚከተሉህም ሕዝብ ሁሉ ከዚያች ምድር ይውጡ እያሉ ወደ እኔ ይወርዳሉ፤ ለእኔም ይሰግዳሉ፤ ከዚያም በኋላ እወጣለሁ።” ሙሴም በጽኑ ቍጣ ከፈርዖን ዘንድ ወጣ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)8 እነዚህም ባሪያዎችህ ሁሉ፥ አንተ ውጣ የሚከተሉህም ሕዝብ ሁሉ ይውጡ እያሉ ወደ እኔ ይወርዳሉ፤ ለእኔም ይሰግዳሉ፤ ከዚያም በኋላ እወጣለሁ።’” ሙሴም በጽኑ ቁጣ ከፈርዖን ዘንድ ወጣ። ምዕራፉን ተመልከት |