ዘፀአት 10:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)14 አንበጣዎችም በግብጽ ምድር ሁሉ ላይ ወጡ፥ በግብጽም አገር ሁሉ ላይ ተቀመጡ፤ እጅግም ብዙ ነበሩ፥ ይህንም የሚያህል አንበጣ በፊት አልነበረም፥ ወደፊትም ደግሞ እንደ እርሱ ያለ አይሆንም። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም14 እነርሱም ግብጽን በሙሉ ወረሩ፤ ስፍር ቍጥር የሌላቸው ሆነው የሀገሪቱን ዳር ድንበር ሁሉ አለበሱ። እንዲህ ያለ የአንበጣ መዓት ከዚህ ቀደም አልነበረም፤ ወደ ፊትም ደግሞ አይኖርም። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም14 እነርሱም በመርመስመስ መጥተው አገሪቱን ወረሩ፤ ይህን ያኽል ብዛት ያለው የአንበጣ መንጋ ከዚያ በፊት ታይቶ አይታወቅም፤ ወደ ፊትም ሊታይ አይችልም። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)14 አንበጣም በግብፅ ሀገር ሁሉ ላይ ወጣ፤ በግብፅም ዳርቻ ሁሉ ላይ ተቀመጠ፤ እጅግም ብዙና ጠንካራ ነበር፤ ይህንም የሚያህል አንበጣ በፊት አልነበረም፤ ወደፊትም ደግሞ እንደ እርሱ አይሆንም። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)14 አንበጣዎችም በግብፅ አገር ሁሉ ላይ ወጡ፤ በግብፅም ዳርቻ ሁሉ ላይ ተቀመጡ፤ እጅግም ብዙ ነበሩ፤ ይህንም የሚያህል አንበጣ በፊት አልነበረም፤ ወደፊትም ደግሞ እንደ እርሱ አይሆንም። ምዕራፉን ተመልከት |