ዘፀአት 10:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)1 ጌታም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ወደ ፈርዖን ግባ እኔ ልቡንና የአገልጋዮቹን ልብ ያደነደንኩት በመካከላቸው ምልክቶቼን እንዳሳይ ነው። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም1 ከዚያም እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ተመልሰህ ወደ ፈርዖን ሂድ፤ እነዚህን ታምራዊ ምልክቶች በመካከላቸው ለማድረግ የፈርዖንንና የሹማምቱን ልብ አደንድኛለሁና፤ ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም1 ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “እነሆ እንደገና ወደ ፈርዖን ተመልሰህ ግባ፤ እኔ የእርሱንና የመኳንንቱን ልብ ያደነደንኩት በመካከላቸው እነዚህን ተአምራት ለማድረግ ዐቅጄ ነው፤ ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)1 እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፥ “ወደ ፈርዖን ግባ፤ እኔ የፈርዖንንና የሹሞቹን ልብ አጽንቼአለሁና፥ ተአምራቴ በእነርሱ ላይ በትክክል ይመጣ ዘንድ፤ ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)1 እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ወደ ፈርዖን ግባ፤ በመካከላቸው እነዚህን ተአምራት ለማድረግ የእርሱንና የባሪያዎቹን ልብ አደንድኛለሁ። ምዕራፉን ተመልከት |