Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፀአት 1:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 እርሱም ሕዝቡን እንዲህ አላቸው፦ “እነሆ፥ የእስራኤል ሕዝብ ከእኛ ይልቅ በዝተዋል በርትተውማል፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 እርሱም ሕዝቡን እንዲህ አላቸው፤ “እነሆ፤ እስራኤላውያን በቍጥር በልጠውናል፤ ከእኛም ይልቅ እየበረቱ ነው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 እርሱም ለሕዝቡ እንዲህ አለ፦ “እነሆ፥ እነዚህ እስራኤላውያን ቊጥራቸው በዝቶአል፤ የኀይላቸውም ብርታት አስጊ ሆኖብናል፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 እር​ሱም ሕዝ​ቡን፥ “እነሆ፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሕዝብ ታላ​ቅና ብዙ ሆነ​ዋል፤ ከእ​ኛም ይልቅ በር​ት​ተ​ዋል፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 እርሱም ሕዝቡን፦ “እነሆ፥ የእስራኤል ልጆች ሕዝብ ከእኛ ይልቅ በዝተዋል በርትተውማል፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፀአት 1:9
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ደግሞም የሰውን ድካምና የብልሃት ሥራውን ሁሉ ተመለከትሁ፥ በባልንጀራም ዘንድ ቅንዓት እንደሚያስነሣ አየሁ፥ ይህም ደግሞ ከንቱ ነፋስንም እንደ መከተል ነው።


እኛ ደግሞ አስቀድመን የማናስተውል ነበርንና፤ የማንታዘዝ፥ የምንስት፥ ለምኞትና ለልዩ ልዩ ተድላ እንደ ባርያዎች የምንገዛ፥ በክፋትና በምቀኝነት ጊዜያችንን የምናሳልፍ፥ የምንጠላ፥ እርስ በርሳችንም የምንጠላላ ነበርን።


ቁጣ ጭካኔን ያስከትላል፥ ንዴትም እንደ ጎርፍ ነው፥ በቅንዓት ፊት ግን ማን መቆም ይችላል?


የንጉሥ ክብር በሕዝብ ብዛት ነው፥ በሰው ጥቂትነት ግን የገዥ ጥፋት አለ።


ወይስ “እርሱ በውስጣችን ያሳደረው መንፈስ አብዝቶ ይቀናል” በማለት መጽሐፍ የተናገረው በከንቱ ይመስላችኋልን?


አላዋቂውን ሰው ቁጣ ይገድለዋል፥ ሞኙንም ቅንዓት ያጠፋዋል።


አቢሜሌክም ይስሐቅን፦ “ከእኛ ተለይተህ ሂድ፥ ከእኛ ይልቅ እጅግ በርትተሃልና” አለው።


እሱም አለው፦ “የአባቶችህ አምላክ እግዚአብሔር እኔ ነኝ፥ ወደ ግብጽ መውረድ አትፍራ፥ በዚያ ትልቅ ሕዝብ አደርግሃለሁና።


ፈርዖንም፦ “እነሆ የምድሩ ሕዝብ አሁን በዝቶአል፥ እናንተም ሥራቸውን ታስፈቱአቸዋላችሁ” አለ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች