Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኤፌሶን 4:28 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 የሰረቀ ከእንግዲህ ወዲህ አይስረቅ፤ ነገር ግን በዚያ ፈንታ ለጎደለው የሚያካፍለው እንዲኖረው በገዛ እጆቹ መልካምን እየሠራ ይድከም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 ይሰርቅ የነበረ ከእንግዲህ አይስረቅ፤ ነገር ግን ለተቸገሩት የሚያካፍለው ነገር እንዲኖረው በገዛ እጆቹ በጎ የሆነውን እየሠራ ለማግኘት ይድከም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 ይሰርቅ የነበረ ከእንግዲህ ወዲያ አይስረቅ፤ ይልቅስ ለችግረኞች ይሰጥ ዘንድ ገንዘብ እንዲኖረው በገዛ እጆቹ መልካም ነገርን ይሥራ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 የሚ​ሰ​ር​ቅም እን​ግ​ዲህ አይ​ስ​ረቅ፤ ነገር ግን ድሃ​ውን ይረዳ ዘንድ በእ​ጆቹ መል​ካም እየ​ሠራ ይድ​ከም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 የሰረቀ ከእንግዲህ ወዲህ አይስረቅ፥ ነገር ግን በዚያ ፈንታ ለጎደለው የሚያካፍለው እንዲኖርለት በገዛ እጆቹ መልካምን እየሠራ ይድከም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤፌሶን 4:28
33 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

መልካምን ያድርጉ፥ በበጎም ሥራ ባለ ጠጎች በመሆን ለመለገስና ለማካፈል የተዘጋጁ ይሁኑ፤


ስለዚህ ጊዜ ሳለን ለሰው ሁሉ፥ በተለይም ለእምነት ቤተሰቦች መልካም እናድርግ።


እርሱም እንዲህ አለኝ፦ “ይህ በምድር ፊት ሁሉ ላይ የሚወጣው እርግማን ነው፤ የሚሰርቅና በሐሰት የሚምልም ሁሉ በእዚህ ላይ እንደተጻፈው ይጠፋል።


ይህንንም የተናገረው ለድሆች አዝኖላቸው ሳይሆን ሌባ ስለ ነበረ ነው፤ የገንዘብ ከረጢትም ይዞ በውስጡ ከሚገባው ይወስድ ስለ ነበረ ነው።


ዘኬዎስ ግን ቆሞ ጌታን “ጌታ ሆይ! ካለኝ ሁሉ እኩሌታውን ለድኾች እሰጣለሁ፤ ማንንም በሐሰት ከስሼ እንደሆንሁ አራት እጥፍ እመልሳለሁ፤” አለው።


መራገምና መዋሸት፥ መግደልና መስረቅ፥ ማመንዘርም ገደባቸውን አልፈዋል፤ ደም ማፍሰስ ደም ማፍሰስን አስከትሏል።


ትሰርቃላችሁን፥ ትገድላላችሁን፥ ታመነዝራላችሁን፥ በሐሰትም ትምላላችሁን፥ ለበዓልም ታጥናላችሁን፥ የማታውቋቸውንም እንግዶች አማልክት ትከተላላችሁን፤


“የባልንጀራህን ቤት አትመኝ፤ የባልንጀራህን ሚስት፥ ወንድ ሠራተኛውን፥ ሴት ሠራተኛውን፥ በሬውን፥ አህያውን፥ የባልንጀራህ የሆነውን ሁሉ ማናቸውንም አትመኝ።”


በጎ ፈቃድ ቢኖር፥ ባለው ባለው መጠን ተቀባይነት ይኖረዋል እንጂ የሌላውን አይጠበቅበትም።


በብዙ መከራ እየተፈተኑም ቢሆን ደስታቸው እጥፍ ድርብ ነበር፤ የድህነታቸው መጠን ቢበዛም ልግስናቸው የበዛ ነበር።


ቅዱሳንን በሚያስፈልጋቸው እርዱ፤ እንግዶችን ተቀበሉ።


ይሁዳ የገንዘብ ከረጢቱን ይዞ ስለ ነበር፥ አንዳንዶቹ ኢየሱስ “ለበዓሉ የሚያስፈልገንን ግዛ፤ ወይም ለድሆች ምጽዋት ስጥ” ያለው መስሎአቸው ነበርና።


እንግዲህ ለንስሓ የሚገቡ ፍሬዎች አፍሩ፤ በልባችሁም ‘አብርሃም አባት አለን፤’ አትበሉ፤ ከእነዚህ ድንጋዮች ለአብርሃም ልጆች ሊያስነሣለት እግዚአብሔር እንደሚችል እነግራችኋለሁና።


እንዳልጠግብ እንዳልክድህም፦ “ጌታስ ማን ነው?” እንዳልል፥ ድሀም እንዳልሆን እንዳልሰርቅም፥ የአምላኬንም ስም እንዳላረክስ።


ጥፋቱን የሚሰውር አይለማም፥ የሚናዘዝባትና የሚተዋት ግን ምሕረትን ያገኛል።


በድካም ሁሉ ልምላሜ ይገኛል፥ ብዙ ነገር በሚናገር ከንፈር ግን ድህነት ብቻ አለ።


በችኰላ የምትከማች ሀብት ትጐድላለች፥ ጥቂት በጥቂት የተከማቸች ግን ትበዛለች።


የማላየውን ነገር አንተ አስተምረኝ፥ ኃጢአትንም ሠርቼ እንደሆነ፥ ደግሜ አልሠራም የሚለው ማን ነው?


ሰውን ሰርቆ ቢሸጥ፥ ወይም በእጁ ቢገኝ፥ ፈጽሞ ይሙት።


ኀጥእ ቀኑን ሁሉ ምኞትን ይመኛል፥ ጻድቅ ግን ይሰጣል፥ አይሰስትም።


እጅዋን ወደ ድሀ ትዘረጋለች፥ ወደ ችግረኛም እጅዋን ትሰድዳለች።


በገዛ እጃችን እየሠራን እንደክማለን፤ ሲረግሙን እንመርቃለን፤ ሲያሳድዱን እንታገሣለን፤


ቃሉ የታመነ ነው። እግዚአብሔርንም የሚያምኑት በመልካም ሥራ በጥንቃቄ እንዲተጉ፥ እነዚህን አስረግጠህ እንድትናገር እፈቅዳለሁ። ይህ መልካምና ለሰዎች የሚጠቅም ነው፤


ከእኛም ወገን የሆኑ ሰዎች ደግሞ ፍሬ ቢሶች ሆነው እንዳይቀሩ፥ የግድ ስለሚያስፈልገው ነገር መልካም ሥራን ተግተው መሥራትን ይማሩ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች