Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኤፌሶን 4:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ከእንግዲህ እንደ ስሕተት ሽንገላ ባለ ተንኮል፥ በሰዎችም ማታለል ምክንያት፥ በነፈሰው የትምህርት ነፋስ ሁሉ እየተፍገመገምን፥ ወዲያና ወዲህም እየተንሳፈፍን፥ ሕፃናት መሆን አይገባንም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ከእንግዲህ በማዕበል ወደ ፊትና ወደ ኋላ እየተነዳን፣ በልዩ ልዩ ዐይነት የትምህርት ነፋስ፣ በሰዎችም ረቂቅ ተንኰልና ማታለል ወዲያና ወዲህ እየተንገዋለልን ሕፃናት አንሆንም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ከእንግዲህ ወዲህ በሰዎች የተንኰል ሽንገላና አታላይነት በተዘጋጀ በአሳሳች የትምህርት ነፋስና ሞገድ ወዲያና ወዲህ ተገፍትረው እንደሚወሰዱ ሕፃናት አንሆንም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 እን​ግ​ዲህ በሽ​ን​ገ​ላ​ቸው ያስቱ ዘንድ በሚ​ተ​ና​ኰሉ ሰዎች ተን​ኰል ምክ​ን​ያት በት​ም​ህ​ርት ነፋስ ሁሉ ወዲ​ያና ወዲህ እየ​ተ​ፍ​ገ​መ​ገ​ም​ንና እየ​ተ​ን​ሳ​ፈ​ፍን ሕፃ​ናት አን​ሁን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 እንደ ስሕተት ሽንገላ ባለ ተንኮል በሰዎችም ማታለል ምክንያት በትምህርት ነፋስ ሁሉ እየተፍገመገምን ወዲያና ወዲህም እየተንሳፈፍን ሕፃናት መሆን ወደ ፊት አይገባንም፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤፌሶን 4:14
44 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በልዩ ልዩ እንግዳ ትምህርት አትወሰዱ፤ መልካም የሚሆነው ልባችሁ በጸጋ ቢጸና ነው እንጂ በመብል አይደለም፤ በዚህ የሚኖሩትም እንኳን አልተጠቀሙም።


ወንድሞች ሆይ፤ በአስተሳሰባችሁ ሕፃናት አትሁኑ፤ ለክፉ ነገር ሕፃናት ሁኑ እንጂ በአስተሳሰባችሁ ግን ጐልማሶች ሁኑ።


ወዳጆች ሆይ፥ መንፈስን ሁሉ አትመኑ፥ ነገር ግን መንፈሶች ከእግዚአብሔር መሆናቸውን መርምሩ፤ ብዙ ሐሰተኞች ነቢያት ወደ ዓለም መጥተዋልና።


የእግዚአብሔርን ቃል ቀላቅለው እንደሚነግዱ እንደ ብዙዎቹ አይደለንም፤ በቅንነት ግን ከእግዚአብሔር እንደ ተላክን በእግዚአብሔር ፊት በክርስቶስ ሆነን እንናገራለን።


ነገር ግን በምንም ሳይጠራጠር በእምነት ይለምን፤ ምክንያቱም የሚጠራጠር ሰው በነፋስ እንደሚገፋና እንደሚነዋወጥ የባሕርን ማዕበል ነው።


የዲያብሎስን ሽንገላ ለመቃወም እንድትችሉ፥ የእግዚአብሔርን ሙሉ የጦር ትጥቅ ልበሱ።


ሐሰተኞች መሲሖችና ሐሰተኞች ነቢያት ይነሣሉና፤ ቢቻላቸውስ የተመረጡትን እንኳ ለማሳት ታላላቅ ምልክትንና ድንቅ ነገሮችን ያሳያሉ።


ሰዎች እውነተኛውን ትምህርት የማይታገሱበት፤ ይልቁንም ጆሮዎቻቸውን የሚኮረኩራቸውን ነገር በመሻት ለራሳቸው ምኞት የሚመቹ አስተማሪዎችን የሚሰበስቡበት ጊዜ ይመጣልና።


እነዚህ በፍቅር ግብዣችሁ ላይ ነውር ናቸው፥ ራሳቸውን እየመገቡ ያለ ኀፍረት ከእናንተ ጋር ይጋበዛሉ፥ በነፋስ የሚገፉ ውሃ የሌላቸው ደመናዎች፥ በበጋ ፍሬ የማያፈሩ፥ ሁለት ጊዜ የሞቱ፥ ከሥራቸው የተነቀሉ ዛፎች ናቸው፤


አውሬውም ተያዘ፤ በእርሱም ፊት ተአምራትን እያደረገ የአውሬውን ምልክት የተቀበሉትን ለምስሉም የሰገዱትን ያሳተ ሐሰተኛውም ነቢይ ከእርሱ ጋር ተያዘ፤ ሁለቱም በሕይወት ሳሉ በዲን ወደሚቃጠል ወደ እሳት ባሕር ተጣሉ።


እናንተ የማታስተውሉ የገላትያ ሰዎች ሆይ! ማን መተት አደረገባችሁ? ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ተሰቀለ ሆኖ በዐይኖቻችሁ ላይ ተሥሎ ነበር፤


ብዙ ሐሰተኞች ነቢያት ይነሣሉ፤ ብዙዎችንም ያስታሉ፤


ስለሚያታልሉአችሁ ሰዎች ይህን ጽፌላችኋለሁ።


ነገር ግን ክፉዎች ሰዎችና አስመሳዮች እያታለሉና እየተታለሉ ከክፋት ወደ ባሰ ክፋት ይሄዳሉ።


“እውቀትን ለማን ያስተምረዋል? ወይስ ወሬ ማስተዋልን ለማን ይሰጣል? ወተትን ለተዉ ወይስ ጡትን ለጣሉ ነውን?”


የሚያሳፍረውን ስውር ነገር ጥለናል፤ በተንኮል አንመላለስም ወይም የእግዚአብሔርን ቃል በውሸት አንቀላቅልም፤ እውነትን በመግለጥ ግን በእግዚአብሔር ፊት ለሰው ሕሊና ሁሉ ራሳችንን እናቀርባለን።


እነርሱ ከሄዱ በኋላ ኢየሱስ ለሕዝቡ ስለ ዮሐንስ እንዲህ ሲል መናገር ጀመረ “ወደ ምድረ በዳ ምን ልታዩ ወጣችሁ? በነፋስ የሚወዛወዘውን ሸምበቆ?


አሕዛብ በነበራችሁበት ጊዜ በማታውቁት ነገር ተመርታችሁ መናገር ወደማይችሉ ጣዖቶች ትወሰዱ እንደ ነበር ታውቃላችሁ።


እንግዲህ አንተ በጅ አትበላቸው፤ እስኪገድሉት ድረስ እንዳይበሉና እንዳይጠጡ ተማምለው ከእነርሱ ከአርባ የሚበዙ ሰዎች ያደቡበታልና፤ አሁንም የተዘጋጁ ናቸው፤ የአንተንም ምላሽ ይጠብቃሉ፤” አለው።


ታማኝ ሰው ከምድሪቱ ጠፍቶአል፥ በሰው መካከል ቅን የለም፤ ሁሉም ለደም ያደባሉ፥ እያንዳንዱም ወንድሙን በመረብ ያጠምዳል።


ከግፍ አድራጊዎች ታደገኝ፥ ከደም ሰዎችም አድነኝ።


እንደ አንበሳ በዱር በስውር ይሸምቃል፥ ድሀውን ለመንጠቅ ያደባል፥ ድሀውን ይነጥቀዋል በአሽክላውም ይስበዋል።


ከእኛ ዘንድ ወጡ፥ ነገር ግን ከእኛ ወገን አልነበሩም፤ ከእኛ ወገንስ ቢሆኑ ኖሮ ከእኛ ጋር በኖሩ ነበር፤ ነገር ግን ሁሉ ከእኛ ወገን እንዳልሆኑ እንዲገለጥ ወጡ።


ከንቱና የትዕቢት ቃል ይናገራሉና፤ በስሕተትም ከሚኖሩት ለጥቂት ያመለጡትን ሰዎች በሥጋ ሴሰኛ ምኞት በማታለል ያስታሉ።


መርከቦችንም ተመልከቱ፤ ምንም እንኳ እጅግ ትልቅና በኀይለኛ ነፋስ የሚነዱ ቢሆኑም የመርከቡ ነጂ በትንሽ መሪ ወደሚፈልገው አቅጣጫ ይመራቸዋል።


በትዕቢት ተወጥሮ በዲያቢሎስ ፍርድ እንዳይወድቅ፥ አዲስ ክርስቲያን አይሁን።


በእስያ ያሉት ሁሉ ከእኔ ዘወር ብለው እንደ ሄዱ ታውቃለህ፤ ከእነርሱም መካከል ፊሎጎስና ሄርዋጌኔስ ይገኛሉ።


የዚህ ዓለም ጥበብ በእግዚአብሔር ዘንድ ሞኝነት ነው። እንደተጻፈውም፥ “እርሱ ጥበበኞችን በተንኰላቸው ይይዛቸዋል፤”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች