መክብብ 9:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)1 ጻድቃንና ጠቢባን፥ ሥራዎቻቸውም በእግዚአብሔር እጅ እንደ ሆኑ፥ ይህን ሁሉ እመረምር ዘንድ በልቤ አኖርሁ፥ ፍቅርም ሆነ ጥል ቢሆን ሰው አያውቅም፤ ሁሉም በፊታቸው ነው። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም1 ስለዚህ ይህን ሁሉ በልቤ አስቤ እንዲህ አልሁ፤ ጻድቃንና ጠቢባን የሚሠሩትም ሥራ በአምላክ እጅ ነው፤ ነገር ግን ፍቅር ይሁን ወይም ጥላቻ የሚጠብቀውን ማንም አያውቅም። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም1 ስለ ነዚህ ሁሉ ነገሮች ለረጅም ጊዜ በብርቱ ካሰብኩ በኋላ የደጋግና የጥበበኞች ሰዎችን ሥራ በእግዚአብሔር እጅ እንደ ሆነ ተረዳሁ፤ ስለዚህ ወደፊት የሚገጥመውን ነገር ፍቅርም ሆነ ጥላቻ አስቀድሞ የሚያውቅ ሰው የለም። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)1 ይህን ሁሉ በአንድነት ለልቤ ሰጠሁ፥ ጻድቃንና ጠቢባን ሥራዎቻቸውም በእግዚአብሔር እጅ እንደ ሆኑ፥ ይህን ሁሉ ልቤ ተመለከተች፤ ፍቅር ወይም ጥል ቢሆን ሰው አያውቅም፥ ሁሉ ወደ ፊታቸው ነው። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)1 ጻድቃንና ጠቢባን ሥራዎቻቸውም በእግዚአብሔር እጅ እንደ ሆኑ፥ ይህን ሁሉ እመረምር ዘንድ በልቤ አኖርሁ፥ ፍቅር ወይም ጥል ቢሆን ሰው አያውቅም ሁሉ ወደ ፊታቸው ነው። ምዕራፉን ተመልከት |