መክብብ 8:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)7 የሚሆነውንም አያውቅም፥ እንዴትስ እንደሚሆን የሚነግረው ማን ነው? ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም7 ሰው የወደ ፊቱን ስለማያውቅ፣ ሊመጣ ያለውን ማን ሊነግረው ይችላል? ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም7 ወደፊት የሚሆነውን ነገር ለይቶ የሚያውቅ ሰው የለም፤ “ይህ ይሆናል” ብሎ የሚነግረውስ ማነው? ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)7 የሚሆነውንም ምንም የሚያውቅ የለም፤ እንዴትስ እንደሚሆን የሚነግረው ማን ነው? ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)7 የሚሆነውንም አያውቅም፥ እንዴትስ እንደሚሆን የሚነግረው ማን ነው? ምዕራፉን ተመልከት |
መከራቸው ድንገት ይነሣልና፥ ከሁለቱ የሚመጣውን ጥፋት ማን ያውቃል? (የሚቀጥለው ከግሪክ የተጨመረ ነው።) የነገሩትን የሚሰማ ልጅ ከጥፋት የራቀ ነው፥ የነገሩትን የሚቀበልን ሰው እግዚአብሔር ይቀበለዋል። ከንጉሥ አንደበት ምንምን ሐሰት ይነገራል አይባልም፥ ከአንደበቱም የሚወጣ ሐሰት የለም። የንጉሥ ቃል ሾተል ናት፥ ለጥፋት የተሰጠችውን ሰው ሰውነት ታጠፋዋለች እንጂ አንድ አካል ብቻ የምታጠፋ አይደለም። ሰይፈ መዓቱ ብትሳል ግን ከወገኑ ጋር ሰውን ታጠፋለች፥ ከአሞሮች ግልገል ወገን የማይበላ እስኪሆን ድረስ እንደ እሳት ነበልባል ታቃጥላለች።