Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




መክብብ 6:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ለሺህ ዓመት ሁለት ጊዜ በሕይወት ቢኖር፥ ነገር ግን መልካምን ባያይ፥ ሁሉም ወደ አንድ ስፍራ ይሄድ የለምን?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ሁለት ጊዜ ሺሕ ዓመት ቢኖር፣ ነገር ግን በሀብቱ ደስ ባይሠኝበት፣ ሁሉ ወደዚያ ስፍራ የሚሄድ አይደለምን?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ስለዚህ ሁለት ሺህ ዓመት ያለ ደስታ ቢኖር ጥቅሙ ምንድን ነው? ዞሮ ዞሮ ሁለቱም የሚሄዱት ወደ አንድ ተመሳሳይ ስፍራ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ሺህ ዓመት ሁለት ጊዜ በሕ​ይ​ወት ቢኖር፥ መል​ካ​ም​ንም ባያይ፥ ሁሉ ወደ አንድ ስፍራ የሚ​ሄድ አይ​ደ​ለ​ምን?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ሺህ ዓመት ሁለት ጊዜ በሕይወት ቢኖር መልካምንም ባያይ፥ ሁሉ ወደ አንድ ስፍራ የሚሄድ አይደለምን?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መክብብ 6:6
18 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሁሉ ወደ አንድ ቦታ ይሄዳል፥ ሁሉም ከአፈር ነው ሁሉም ወደ አፈር ይመለሳል።


ለሰዎችም አንድ ጊዜ ለመሞት ከዚያም ለፍርድ መቅረብ ተመድቦባቸዋል።


ለሞት፥ ሕያዋንም ሁሉ ለሚሰበሰቡበት ቤት አሳልፈህ እንደምትሰጠኝ አውቄአለሁና።”


እርሱ በምድረ በዳ እንዳለ ቁጥቋጦ ነው፥ መልካምም በመጣ ጊዜ አያይም፤ ሰውም በማይቀመጥበት፥ ጨው ባለበት ምድር፥ በምድረ በዳ በደርቅ ስፍራ ይቀመጣል።


ሌላ እንዲቀመጥበት አይሠሩም፥ ሌላም እንዲበላው አይተከሉም፤ የሕዝቤ ዕድሜ እንደ ዛፍ ዕድሜ ይሆናልና፥ እኔም የመረጥኋቸው በእጃቸው ሥራ ረጅም ዘመን ደስ ይላቸዋል።


ከዚያም ወዲያ ጥቂት ዘመን ብቻ የሚኖር ሕፃን፥ ወይም ዕድሜውን ያልፈጸመ ሽማግሌ አይገኝም፤ ጎልማሳው የመቶ ዓመት ሆኖት ይሞታልና፥ የመቶ ዓመት ሳይሆነው የሚሞት እንደተረገመ ኃጢአተኛ ይታያል።


አፈርም ወደ ነበረበት ምድር ሳይመለስ፥ ነፍስም ወደ ሰጠው ወደ እግዚአብሔር ሳይመለስ ፈጣሪህን አስብ።


ሰው መቶ ልጆች ቢወልድ፥ እጅግ ዘመንም በሕይወት ቢኖር፥ ዕድሜውም እጅግ ዓመት ቢሆን፥ ነገር ግን ነፍሱ መልካምን ነገር ባትጠግብ፥ መቃብርንም ባያገኝ፥ ከእርሱ ይልቅ ጭንጋፍ ይሻላል አልሁ።


ልጆቼ ኑ፥ ስሙኝ፥ ጌታን መፍራት አስተምራችኋለሁ።


“ሕይወቴ እስትንፋስ እንደሆነ አስታውስ፥ ዓይኔ መልካም ነገርን ከእንግዲህ ወዲህ አያይም።


እንዲህም አለ፦ “ራቁቴን ከእናቴ ማኅፀን ወጥቻለሁ፥ ራቁቴንም ወደዚያ እመለሳለሁ፥ ጌታ ሰጠ፥ ጌታ ወሰደ፥ የጌታ ስም የተባረከ ይሁን።”


አዳምም የኖረበት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ ሠላሳ ዓመት ሆነ፥ ሞተም።


የጠቢብ ዐይኖች በራሱ ላይ ናቸው፥ አላዋቂ ግን በጨለማ ይሄዳል፥ ሆኖም የሁለቱም መጨረሻቸው አንድ እንደሆነ አስተዋልሁ።


ደግሞም ፀሐይን አላየውም አላወቀውምም፥ ቢሆንም እርሱ ከዚያ ይልቅ ዕረፍት አለው።


ወደ ግብዣ ቤት ከመሄድ ወደ ልቅሶ ቤት መሄድ ይሻላል፥ እርሱ የሰው ሁሉ ፍጻሜ ነውና፥ ሕያውም የሆነ በልቡ ያኖረዋልና።


የጻድቁና የበደለኛው፥ የመልካሙና የክፉው፥ የንጹሑና የርኩሱ፥ መሥዋዕትን የሚሠዋውና የማይሠዋው፥ የሰው ሁሉ ድርሻው አንድ ነው፤ መልካሙ ሰው እንደ ኃጢአተኛው፥ የሚምለው ሰው መሐላን እንደሚፈራው ነው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች