መክብብ 3:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)22 ያም እድል ፈንታው ነውና ሰው በሥራው ደስ ከሚሰኝበት ነገር በቀር ሌላ መልካም ነገር እንደሌለው አየሁ፥ ከእርሱ በኋላስ የሚሆነውንስ ወስዶ ማን ያሳየዋል? ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም22 ስለዚህ ለሰው ዕጣ ፈንታው ስለ ሆነ፣ በሥራው ከመደሰት የተሻለ ነገር እንደሌለው አየሁ፤ ከርሱ በኋላ የሚሆነውንስ ተመልሶ እንዲያይ የሚያደርገው ማን ነው? ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም22 የሰው ዕድል ፈንታ ይኸው ስለ ሆነ በሚሠራው ነገር ደስ ከሚለው በቀር ሌላ የሚያደርገው ምንም ነገር እንደሌለ አስተዋልኩ፤ ከሞተም በኋላ የሚሆነውን ነገር የሚያውቅ ማንም የለም። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)22 ያም ዕድል ፋንታው ነውና ሰው በሥራው ደስ ከሚለው በቀር ሌላ መልካም ነገር እንደሌለው አየሁ፤ ከእርሱ በኋላስ የሚሆነውን ያይ ዘንድ የሚያመጣው ማን ነው? ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)22 ያም እድል ፈንታው ነውና ሰው በሥራው ደስ ከሚለው በቀር ሌላ መልካም ነገር እንደሌለው አየሁ፥ ከእርሱ በኋላስ የሚሆነውን ያይ ዘንድ የሚያመጣው ማን ነው? ምዕራፉን ተመልከት |