መክብብ 3:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)14 እግዚአብሔር የሚያደርገው ሁሉ ለዘለዓለም እንደሚኖር አወቅሁ፥ ምንም የሚጨመርበት ወይም የሚቀነስለት የለም፥ እግዚአብሔርም ሰዎች ይፈሩ ዘንድ አደረገ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም14 አምላክ ያደረገው ሁሉ ለዘላለም እንደሚኖር ዐውቃለሁ፤ በርሱ ላይ ምንም አይጨመርም፤ ከርሱም ምንም አይቀነስም፤ ሰዎች ይፈሩት ዘንድ ይህን አደረገ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም14 እግዚአብሔር የሠራው ነገር ሁሉ ዘለዓለማዊነት እንዳለው ዐውቃለሁ፤ በእርሱ ላይ የሚጨመርበት ወይም ከእርሱ የሚቀነስ ነገር የለም፤ እግዚአብሔር ይህን ያደረገው ሰዎች እርሱን እንዲፈሩት ነው። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)14 እግዚአብሔር ያደረገው ሁሉ ለዘለዓለም እንዲኖር ዐወቅሁ፤ በእነርሱም ላይ መጨመር ከእነርሱም ማጕደል አይቻልም፤ እግዚአብሔርም በፊቱ ይፈሩ ዘንድ አደረገ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)14 እግዚአብሔር ያደረገው ሁሉ ለዘላለም እንዲኖር አወቅሁ፥ ሊጨመርበት ወይም ከእርሱ ሊጐድል አይቻልም፥ እግዚአብሔርም በፊቱ ይፈሩ ዘንድ አደረገ። ምዕራፉን ተመልከት |