Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




መክብብ 3:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ሰው ደስ ከሚሰኝበትና በሕይወቱ ሳለ መልካምን ነገር ከሚፈጽምበት በቀር ሌላ መልካም ነገር እንደሌለ አወቅሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ለሰዎች፣ በሕይወት እያሉ ደስ ከመሠኘትና መልካምን ነገር ከማድረግ የተሻለ ነገር እንደሌለ ዐወቅሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ስለዚህ ሰው በሕይወቱ ሳለ መልካም ነገር ከማድረግና ደስ ከሚለው በቀር ሌላ የተሻለ ነገር እንደሌለ ተረድቼአለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ሰው ደስ ከሚ​ለ​ውና በሕ​ይ​ወቱ ሳለ መል​ካ​ምን ነገር ከሚ​ያ​ደ​ርግ በቀር በው​ስ​ጣ​ቸው መል​ካም ነገር እን​ደ​ሌለ ዐወ​ቅሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ሰው ደስ ከሚለውና በሕይወቱ ሳለ መልካምን ነገር ከሚያደርግ በቀር መልካም ነገር እንደሌለ አወቅሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መክብብ 3:12
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በጌታ ታመን፥ መልካምንም አድርግ፥ በምድርም ተቀመጥ፥ ታምነህም ተሰማራ።


አንተ ጐበዝ፥ በጉብዝናህ ደስ ይበልህ፥ በጉብዝናህም ወራት ልብህን ደስ ይበለው፥ በልብህም መንገድ ዐይኖችህም በሚያዩት ሂድ፥ ዳሩ ግን ስለዚህ ነገር ሁሉ እግዚአብሔር ወደ ፍርድ እንዲያመጣህ እወቅ።


ለሰው በመብላትና በመጠጣት፥ እንዲሁም በመጣር ከሚያገኘው ደስታ የሚሻለው ነገር የለም፥ ይህም ደግሞ ከእግዚአብሔር እጅ እንደተሰጠ አየሁ።


ልቤ በጥበብ እየመራኝ፥ ሰውነቴን በወይን ጠጅ ደስ ለማሰኘት አላዋቂነትንም ለመያዝ በልቤ መረመርሁ፤ ይህም የሰው ልጆች በሕይወታቸው ዘመን ሁሉ ከፀሐይ በታች ሊሠሩት የሚገባ መልካም ነገር ምን እንደሆነ እስካይ ድረስ ነው።


ያም እድል ፈንታው ነውና ሰው በሥራው ደስ ከሚሰኝበት ነገር በቀር ሌላ መልካም ነገር እንደሌለው አየሁ፥ ከእርሱ በኋላስ የሚሆነውንስ ወስዶ ማን ያሳየዋል?


ከመብላትና ከመጠጣት፥ ደስም ከመሰኘት በቀር ለሰው ልጅ ከፀሐይ በታች ሌላ ምንም መልካም ነገር የለውምና እኔ ደስታን አመሰገንሁ፥ ይህም እግዚአብሔር ከፀሐይም በታች በሰጠው በሕይወቱ ዘመን በድካሙ ከእርሱ ጋር ይኖራል።


ጽድቅን የሚያደርገውን፥ በመንገዶችህም የሚያስቡህን ትገናኛቸዋለህ። እኛ ኃጢአት ሠራን፤ እነሆ፥ አንተ ተቈጥተህ ነበር፤ ፊትህን ስለሰወርክብን እኛ ተሳሳትን።


ነገር ግን በውስጥ ያለውን ምጽዋት አድርጋችሁ ስጡ፤ እነሆም፥ ሁሉ ንጹሕ ይሆንላችኋል።


እንዲሁ እየደከማችሁ ድውዮችን ልትረዱና እርሱ ራሱ ‘ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ብፁዕ ነው፤’ እንዳለ የጌታን የኢየሱስን ቃል ልታስቡ ይገባችሁ ዘንድ በሁሉ አሳየኋችሁ።”


አምላክህ ጌታ በሚመርጠው ስፍራ አንተ፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆችህ፥ ወንድና ሴት አገልጋዮችህ፤ በከተሞችህ የሚኖር ሌዋዊም፥ በጌታ በእግዚአብሔር ፊት ትበሉታላችሁ፤ እጅህም በነካው ነገር ሁሉ በጌታ በእግዚአብሔር ፊት ደስ ይልሃል።


በዚያም በጌታ በአምላካችሁ ፊት ትበላላችሁ፤ ጌታ አምላካችሁ እናንተን በባረከበት፥ በምታደርጉት ሁሉ አንተና ቤተሰቦችህ ሐሤት ታደርጋላችሁ።”


አንተም በመካከልህም ያለ ሌዋዊና መጻተኛ ጌታ እግዚአብሔር ለአንተና ለቤትህ በሰጠው ቸርነት ሁሉ ደስ ይበላችሁ።


ጌታ እናንተን በማበልጸግና ቁጥራችሁን በማብዛት ደስ ይለው እንደ ነበረ፥ እንዲሁ ጌታ እናንተን ሲያጠፋችሁና ሲያፈራርሳችሁም ደስ ይለዋል፤ እንድትወርሱአት ከምትገቡባት ምድር ትነቀላላችሁ።


መልካምን ያድርጉ፥ በበጎም ሥራ ባለ ጠጎች በመሆን ለመለገስና ለማካፈል የተዘጋጁ ይሁኑ፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች