መክብብ 2:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)8 ብርንና ወርቅን የከበረውንም የነገሥታትና የአውራጆችን መዝገብ ሰበሰብሁ፥ ወንዶችና ሴቶች አዝማሪዎችን፥ ለሰዎች ልጆች ተድላ የሚሰጡ እጅግ የበዙ ሴቶችንም አከማቸሁ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም8 ለራሴም ብርንና ወርቅን፣ የነገሥታትና የአውራጃዎችን ሀብት አካበትሁ፤ ወንድና ሴት አዝማሪዎች፣ የሰው መደሰቻ የሆኑ ቅምጦች ነበሩኝ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም8 እኔ በምገዛው አገር ሁሉ ከልዩ ልዩ አውራጃዎች የከበሩ የቤተ መንግሥት መዛግብትን በመሰብሰብ ብዙ ወርቅና ብር አከማቸሁ፤ እኔን የሚያሞግሡ ወንዶችና ሴቶች አዝማሪዎችንም አዘጋጀሁ፤ ለሰው ተድላና ደስታን ሊሰጡ የሚችሉ እጅግ ብዙ ሴቶችንም ሰበሰብኩ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)8 ብርንና ወርቅን፥ የከበረውንም የነገሥታትንና የአውራጆችን መዝገብ ለራሴ ሰበሰብሁ፤ ሴቶችና ወንዶች አዝማሪዎችን፥ የሰዎች ልጆችንም ተድላ አደረግሁ፤ የወይን ጠጅ ጠማቂዎችንና አሳላፊዎችንም አበዛሁ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)8 ብርንና ወርቅን የከበረውንም የነገሥታትና የአውራጆችን መዝገብ ሰበሰብሁ፥ አዝማሪዎችንና አርሆዎችን የሰዎች ልጆችንም ተድላ እጅግ የበዙ ሴቶችንም አከማቸሁ። ምዕራፉን ተመልከት |