Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




መክብብ 2:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ጠቢብ ወይም አላዋቂ እንደሚሆን የሚያውቅ ሰው ማን ነው? ከፀሐይ በታች በደከምሁበትና ጠቢብ በሆንሁበት በድካሜ ሁሉ ላይ ይሠለጥንበታል፥ ይህም ደግሞ ከንቱ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 እርሱ ጠቢብ ወይም ሞኝ ይሆን እንደ ሆነ ማን ያውቃል? ሆኖም ከፀሓይ በታች ድካሜንና ችሎታዬን ባፈሰስሁበት ሥራ ሁሉ ላይ ባለቤት ይሆንበታል፤ ይህም ደግሞ ከንቱ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ከእኔ በኋላ የሚመጣው ጠቢብ ይሁን ሞኝ ተለይቶ አይታወቅም፤ ይሁን እንጂ እኔ የደከምኩበትንና በጥበቤ ያተረፍኩትን ነገር ሁሉ ወስዶ ባለቤት ይሆናል፤ ይህም ከንቱ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ጠቢብ ወይም አላ​ዋቂ እን​ደ​ሚ​ሆን ከፀ​ሐይ በታ​ችም በደ​ከ​ም​ሁ​በ​ትና ጠቢብ በሆ​ን​ሁ​በት በድ​ካሜ ሁሉ ይሰ​ለ​ጥን እንደ ሆነ የሚ​ያ​ውቅ ሰው ማን ነው? ይህም ደግሞ ከንቱ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ጠቢብ ወይም ሰነፍ እንዲሆን የሚያውቅ ሰው ማን ነው? ከፀሐይ በታች በደከምሁበትና ጠቢብ በሆንሁበት በድካሜ ሁሉ ላይ ጌታ ይሆንበታል፥ ይህም ደግሞ ከንቱ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መክብብ 2:19
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከዚህ በኋላ ሰሎሞን ሞተ፤ በአባቱም በዳዊት ከተማም ተቀበረ፤ ልጁም ሮብዓምም በአባቱ በሰሎሞን እግር ተተክቶ ነገሠ።


ንጉሥ ሮብዓምም ሽማግሌዎቹ የሰጡትን ምክር ውድቅ አድርጎ ሕዝቡን በማመናጨቅ መናገር ጀመረ።


እጄ የሠራቻትን ሥራዬን ሁሉ የደከምሁበትንም ድካሜን ሁሉ ተመለከትሁ፥ እነሆ፥ ሁሉ ከንቱ ነፋስንም እንደ መከተል ነበረ፥ ከፀሐይ በታችም ትርፍ አልነበረም።


እኔም ከፀሐይ በታች በደከምሁበት ድካም ሁሉ ተመልሼ ልቤን ተስፋ አስቈረጥሁት።


ያም እድል ፈንታው ነውና ሰው በሥራው ደስ ከሚሰኝበት ነገር በቀር ሌላ መልካም ነገር እንደሌለው አየሁ፥ ከእርሱ በኋላስ የሚሆነውንስ ወስዶ ማን ያሳየዋል?


ከፀሐይ በታችም ይህን ጥበብ አየሁ፥ እርሷም በእኔ ዘንድ ታላቅ መሰለችኝ።


ጌታውም ዐመፀኛውን መጋቢ ስለ ብልኃቱ አመሰገነው፤ የዚህ ዓለም ልጆች ለትውልዳቸው ከብርሃን ልጆች ይልቅ ብልኆች ናቸውና።


ገንዘብን መውደድ የክፋት ሁሉ ሥር ነውና፤ አንዳንዶች ይህን ሲመኙ ከእምነት ፈቀቅ በማለት መንገዳቸውን ስተው ሄደዋል፥ በብዙም ሥቃይ ራሳቸውን ወግተዋል።


መልካም ስጦታ ሁሉ፥ ፍጹምም በረከት ሁሉ፥ እንደ ጥላ መዘዋወር ወይም መለዋወጥ ከሌለበት ከላይ ከብርሃናት አባት ይወርዳሉ።


ከላይ የሆነችው ጥበብ ግን በመጀመሪያ ንጽሕት ናት፤ ቀጥሎም ሰላም ወዳድ፥ ደግ፥ እሺ ባይ፥ ምሕረትና መልካም ፍሬ የሞላባት፥ ጥርጥርና ግብዝነት የሌለባት ናት።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች