መክብብ 2:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)16 በሚመጣው ዘመን ነገር ሁሉ የተረሳ ይሆናልና ለዘለዓለም የሚሆን የጠቢብና የአላዋቂ መታሰቢያ አይገኝም። አዬ ጉድ! ጠቢብ ከአላዋቂ ጋር እንዴት ይሞታል! ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም16 ጠቢቡም ሰው እንደ ሞኙ ለዘላለም አይታወስምና፤ በሚመጡት ዘመናት ሁለቱም ይረሳሉ። ለካ፣ ጠቢቡም እንደ ሞኙ መሞቱ አይቀርም! ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም16 ጥበበኛንም ሆነ ሞኝን ሁለቱንም ለረጅም ጊዜ የሚያስታውሳቸው አይገኝም፤ በሚመጣው ዘመን ሁላችንም የተረሳን ሆነን እንቀራለን፤ ጥበበኞችም ሆንን ሞኞች፥ ሁላችንንም ሞት ይጠብቀናል። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)16 ለብልህ ከአላዋቂ ጋር ለዘለዓለም መታሰቢያ የለውም፤ እነሆ፥ ዘመን ይመጣልና ሁሉም ይረሳል፤ ብልህስ ከአላዋቂ ጋር እንዴት ይሞታል? ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)16 በሚመጣው ዘመን ነገር ሁሉ የተረሳ ይሆናልና ለዘላለም የሚሆን የጠቢብና የሰነፍ መታሰቢያ አይገኝም። አዬ ጉድ! ጠቢብ ከሰነፍ ጋር እንዴት ይሞታል! ምዕራፉን ተመልከት |