Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




መክብብ 12:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 አፈርም ወደ ነበረበት ምድር ሳይመለስ፥ ነፍስም ወደ ሰጠው ወደ እግዚአብሔር ሳይመለስ ፈጣሪህን አስብ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ዐፈር ወደ መጣበት መሬት ሳይመለስ፣ መንፈስም ወደ ሰጠው ወደ አምላክ ሳይመለስ፣ ፈጣሪህን ዐስብ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ሥጋ ዐፈር ስለ ሆነ ወደ ዐፈር ይመለሳል፤ ነፍስም ወደ ፈጠራት ወደ እግዚአብሔር ትሄዳለች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 አፈ​ርም ወደ ነበ​ረ​በት ምድር ሳይ​መ​ለስ፥ ነፍ​ስም ወደ ሰጠው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሳይ​መ​ለስ በሥ​ጋም በነ​በ​ረ​በት ጊዜ መል​ካም ወይም ክፉ ቢሆን ስለ ሠራው ሁሉ መልስ ሳይ​ሰጥ ፈጣ​ሪ​ህን አስብ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 አፈርም ወደ ነበረበት ምድር ሳይመለስ፥ ነፍስም ወደ ሰጠው ወደ እግዚአብሔር ሳይመለስ ፈጣሪህን አስብ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መክብብ 12:7
23 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ነፍሱ ትወጣለች ወደ መሬቱም ይመለሳል፥ ያንጊዜ እቅዶቹ በሙሉ ይጠፋሉ።


ስለ እስራኤል የተነገረ የጌታ ቃል ይህ ነው። ሰማያትን የዘረጋ፥ ምድርንም የመሠረተ፥ የሰውንም መንፈስ በውስጡ የሠራ ጌታ እንዲህ ይላል፦


“ወደ ወጣህበት መሬት እስክትመለስ ድረስ በግንባርህ ላብ እንጀራን ትበላለህ፥ አፈር ነህና፥ ወደ አፈርም ትመለሳለህ።”


ከዚህ በኋላ ጌታ እግዚአብሔር ሰውን ከምድር አፈር አበጀው፥ በአፍንጫውም የሕይወት እስትንፋስን እፍ አለበት፥ ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ሆነ።


መንፈስም የፈጠርሁትም ነፍስ ከፊቴ እንዳይዝል ለዘለዓለም አልጣላም፥ ሁልጊዜም አልቈጣም።


እነርሱም በግምባራቸው ወድቀው በመስገድ እንዲህ አሉ፦ “አምላክ ሆይ! አንተ የሥጋ ለባሽ ሁሉ መንፈስ አምላክ፥ አንድ ሰው ኃጢአት ቢሠራ አንተ በማኅበሩ ሁሉ ላይ ትቈጣለህን?”


ሰውን ወደ አፈር ትመልሳለህ፥ “የሰው ልጆች ሆይ”፥ ተመለሱ ትላለህ፥


አጥንቶቹ በወጣት ኃይል ተሞልተው ነበር፥ ነገር ግን አሁን ያ የወጣትነት ኃይሉ ከእርሱ ጋር በመሬት ውስጥ ይተኛል።”


የሥጋ ለባሽ ሁሉ መንፈስ አምላክ የሆነ ጌታ በማኅበሩ ላይ አንድ ሰው ይሹም።


በሰማያትም ወደ ተጻፉ ወደ በኵራት ማኅበር፥ የሁሉም ዳኛ ወደሚሆን ወደ እግዚአብሔር፥ ፍጹማንም ወደ ሆኑት ወደ ጻድቃን መንፈሶች፥


ከዚህም በተጨማሪ የቀጡን የሥጋችን አባቶች ነበሩን፤ እናከብራቸውም ነበር፤ ታዲያ እንዴት በላቀ ለመናፍስት አባት አብልጠን ልንገዛና በሕይወት ልንኖር አይገባንም?


ንጉሡም ሴዴቅያስ፦ “ይህችን ነፍስ በፈጠረልን በሕያው ጌታ እምላለሁ! አልገድልህም፥ ነፍስህንም ለሚሹ ለእነዚህ ሰዎች እጅ አሳልፌ አልሰጥህም” ብሎ በድብቅ ለኤርምያስ ማለ።


አብርሃምም መለሰ ዓለም፦ “እኔ አፈርና አመድ ስሆን ከጌታዬ ጋር እናገር ዘንድ እነሆ አንድ ጊዜ ጀመርሁ፥


ስለምን መተላለፌን ይቅር አትልም? ኃጢአቴንስ ስለምን አታስወግድልኝም? አሁን በምድር ውስጥ እተኛለሁ፥ ትፈልገኛለህ፥ እኔ ግን የለሁም።”


ኢየሱስም በታላቅ ድምፅ ጮኾ “አባት ሆይ! ነፍሴን በእጅህ አደራ እሰጣለሁ፤” አለ። ይህንንም ብሎ ሞተ።


እስጢፋኖስም “ጌታ ኢየሱስ ሆይ! ነፍሴን ተቀበል፤” ብሎ ሲጠራ ይወግሩት ነበር።


ፍጥረታችንን እርሱ ያውቃልና፥ እኛ አፈር እንደ ሆንን ያስታውሳል።


ፊትህን ስትሰውር ይደነግጣሉ፥ ነፍሳቸውን ታወጣለህ ይሞታሉም፥ ወደ አፈራቸውም ይመለሳሉ።


በእጅህ ነፍሴን አደራ እሰጣለሁ፥ የእውነት አምላክ አቤቱ፥ ተቤዥተኸኛል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች