Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




መክብብ 12:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 የወፍጮ ድምፅ ሲላሽ፥ ከወፍ ድምፅ የተነሣ ሰው ሲነሣ፥ ዜማም የሚጮኹ ሴቶች ልጆች ሁሉ ዝግ ሲሉ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ወደ አደባባይ የሚያወጡ በሮች ሲዘጉ፣ ወፍጮ ሟልጦ ድምፁ ሲላሽ፣ ሰው በወፍ ድምፅ ሲነሣ፣ ዝማሬው ሁሉ ሲዳከም፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ጆሮችህ የአደባባይ ጫጫታ አይሰሙም የወፍጮ ወይም የሙዚቃ ድምፅ መስማት ይሳንሃል፤ ሆኖም የወፍ ድምፅ እንኳ ከእንቅልፍህ ይቀሰቅስሃል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 በአ​ደ​ባ​ባ​ይም ደጆቹ በሚ​ዘ​ጉ​በት ቀን፥ የወ​ፍጮ ድምፅ ሲላሽ፥ ከዎፍ ድምፅ የተ​ነሣ ሰው ሲነሣ፥ ዜማም የሚ​ጮኹ ሴቶች ልጆች ሁሉ ዝግ ሲሉ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 የወፍጮ ድምፅ ሲላሽ፥ ከወፍ ድምፅ የተነሣ ሰው ሲነሣ፥ ዜማም የሚጮኹ ሴቶች ልጆች ሁሉ ዝግ ሲሉ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መክብብ 12:4
5 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከእነርሱም የእልልታን ድምፅና የደስታን ድምፅ፥ የሙሽራውን ድምፅና የሙሽራይቱን ድምፅ፥ የወፍጮንም ድምፅ የመብራትንም ብርሃን አስቀራለሁ።


ባርዚላይ ግን ለንጉሡ እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “ከንጉሡ ጋር ወደ ኢየሩሳሌም የምሄደው ለየትኛው ዕድሜዬ ብዬ ነው?


ከእንግዲህ ወዲህ በገና የሚመቱና የሚዘምሩ ሰዎች ድምፅ፥ እንቢልታንና መለከትንም የሚነፉ ሰዎች ድምፅ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይሰማም፤ የማንኛውም ዕደ ጥበብ ብልሃተኛ ሰው ከእንግዲህ ወዲህ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይገኝም፤ የወፍጮ ድምጽም ከእንግዲህ ወዲህ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይሰማም፤


ወፍጮ ወስደሽ ዱቄትን ፍጪ፤ መሸፈኛሽን አውጪ ረጅሙንም ልብስሽን አውልቀሽ ጣይው፤ ባትሽን ግለጪ፥ ወንዙን ተሻገሪ።


አንገቱ በጣም ጠንካራ ነው፥ ግርማ በፊቱ ይዘፍናል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች