Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘዳግም 9:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 እግዚአብሔር ሊያጠፋችሁ በመነሳቱ ከቁጣውና ከመዓቱ የተነሣ ፈራሁ። ጌታ ግን ልመናዬን ደግሞ ሰማኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 እናንተን ሊያጠፋችሁ ክፉኛ ተቈጥቶ ነበርና፣ እኔም የእግዚአብሔርን ቍጣና መዓት ፈራሁ፤ እግዚአብሔር ግን እንደ ገና ሰማኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 በመዓቱም ሊደመስሳችሁ ስለ ተነሣሣ የእግዚአብሔር ብርቱ ቊጣ አስፈርቶኝ ነበር፤ ነገር ግን እንደገና እግዚአብሔር ልመናዬን ሰማ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሊያ​ጠ​ፋ​ችሁ ከተ​ቈ​ጣ​ባ​ችሁ ከቍ​ጣ​ውና ከመ​ዓቱ የተ​ነሣ ፈራሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በዚ​ያን ጊዜ ደግሞ ሰማኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘዳግም 9:19
19 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“እኔም፥ ከዚህ ቀደም እንዳደረኩት፥ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በተራራው ላይ ተቀመጥሁ፥ በዚህም ጊዜ ጌታ ደግሞ ሰማኝ፤ ጌታ ሊያጠፋህ አልወደደም።


ሙሴና አሮን በካህናቱ ዘንድ፥ ሳሙኤልም ስሙን በሚጠሩት ዘንድ ናቸው፥ ጌታን ጠሩት፥ እርሱም መለሰላቸው።


ጌታ ሙሴን፦ “በፊቴ ሞገስን ስላገኘህና በስምህም ስላወቅሁህ ይህን ያልኸውን ነገር ሁሉ አደርጋለሁ” አለው።


ጌታም በሕዝቡ ላይ አደርጋለሁ ያለውን ክፋ ነገር መለሰ።


እንዳያጠፋቸው ቁጣውን ይመልስ ዘንድ የተመረጠው ሙሴ በመቅሠፍት ጊዜ በፊቱ ባይቆም ኖሮ፥ ያጠፋቸው እንደ ነበረ ተናገረ።


በኮሬብም የጌታን ቁጣ ቀሰቀሳችሁ፥ ጌታም ሊያጠፋችሁ እስኪነሳ አስቆጣችሁት።


ሙሴም “እጅግ እፈራለሁ፤ እንቀጠቀጥማለሁ፤” እስኪል ድረስ የሚታየው ነገር እጅግ የሚያስፈራ ነበር፤


እርሱም እንዲህ አለው፦ “እነሆ እኔ ቃል ኪዳን አደርጋለሁ፤ በምድር ሁሉና በአሕዛብ ሁሉ ዘንድ እንደ እርሱ ያለ ከቶ ያልተደረገ ተአምራት ፊት አደርጋለሁ፤ እኔ በአንተ የምሠራው ነገር የሚያስፈራ ነውና በመካከላቸው የምትኖርባቸው ሕዝብ ሁሉ የጌታን ሥራ ያያል።


ጌታ አሮንንም እጅግ ተቆጥቶ ሊያጠፋው ስለ ነበር፥ በዚያን ጊዜ ስለ አሮንም ደግሞ ጸለይሁ።


የጌታም ቁጣ በላያችሁ እንዳይነድ፤ እርሱም ዝናብ እንዳይከለክላችሁ፤ ምድሪቱም ፍሬ እንዳትሰጥ ሰማያትን ይዘጋል፤ እናንተም ጌታ ከሚሰጣችሁ ከመልካሚቱ ምድር ወዲያውኑ ትጠፋላችሁ።”


እግዚአብሔርም ይህን ሰምቶ ተቈጣ፥ እስራኤልንም ፈጽሞ ተወ፥


ሕዝቡም ወደ ሙሴ ጮኹ፤ ሙሴም ወደ ጌታ ጸለየ፥ እሳቱም ጠፋ።


በኮሬብም ጥጃን ሠሩ፥ ቀልጦ ለተሠራ ምስልም ሰገዱ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች