Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘዳግም 6:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 እርሱም እንዳዘዘን በጌታ አምላካችን ፊት እነዚህን ትእዛዛት ሁሉ ለመፈጸም ብንጠነቀቅ ለእኛ ጽድቅ ይሆንልናል።’

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 እንግዲህ ይህን ሁሉ ሕግ እርሱ ባዘዘን መሠረት፣ በአምላካችን በእግዚአብሔር ፊት ተጠንቅቀን ከጠበቅን፣ ያ ለእኛ ጽድቃችን ይሆናል።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 እግዚአብሔር አምላካችን እንዳዘዘን የእርሱን ትእዛዞች ሁሉ በጥንቃቄ ብንፈጽም ለእኛ ጽድቅ ይሆንልናል።’

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዳ​ዘ​ዘን በአ​ም​ላ​ካ​ችን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እና​ደ​ር​ጋት ዘንድ ይህ​ችን ትእ​ዛዝ ሁሉ ብን​ጠ​ብቅ ለእኛ ምሕ​ረት ይሆ​ን​ል​ናል።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 እርሱም እንዳዘዘን በአምላካችን በእግዚአብሔር ፊት እናደርጋት ዘንድ ይህችን ትእዛዝ ሁሉ ብንጠብቅ ለእኛ ጽድቅ ይሆንልናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘዳግም 6:25
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ትእዛዞችህንም ሁሉ ስመለከት በዚያን ጊዜ አላፍርምና።


ተስፋቸውን በእግዚአብሔር እንዲያደርጉ፥ የእግዚአብሔርንም ሥራ እንዳይረሱ፥ ትእዛዙንም እንዲጠብቁ፥


በጽድቅ መንገድ ላይ ሕይወት አለ በጎዳናዋም ሞት የለም።


በትእዛዜ ቢሄድ፥ እውነትን ለማድረግ ፍርዴን ቢጠብቅ፥ እርሱ ጻድቅ ነው፥ ፈጽሞ በሕይወት ይኖራል፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


ሰው ቢያደርገው ኖሮ በሕይወት የሚኖርበትን ሥርዓቴንም ሰጠኋቸው፥ ፍርዴንም አስታወቅኋቸው።


ስለዚህ ሥርዓቴንና ፍርዴን ጠብቁ፥ እነርሱን የሚያደርግ ሰው በእነርሱ በሕይወት ይኖራልና፤ እኔ ጌታ ነኝ።


የእግዚአብሔርን ጽድቅ ባለማወቅ፥ የራሳቸውንም ጽድቅ ለመመሥረት በመፈለግ፥ ለእግዚአብሔር ጽድቅ አልተገዙም።


ሕግ ከእምነት አይደለም፤ ነገር ግን “የሚፈጽማቸው በእነርሱ ይኖራል።”


መደረቢያውን ለብሶት እንዲያድር ፀሓይ ሳትጠልቅ መልስለት። ከዚያም ያመሰግንሃል፤ በጌታ በእግዚአብሔር ፊትም የጽድቅ ሥራ ሆኖ ይቆጠርልሃል።


ምክንያቱም ሕግን ሁሉ ብትፈጽሙ ነገር ግን በአንዱ ብትሰናከሉ፥ ሁሉን እንደ ተላለፋችሁ ይቈጠራል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች