Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -






ዘዳግም 5:17
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“አታመንዝር፤ አትግደል፤ አትስረቅ፤ አትመኝ፤” የሚለው እና ሌላም ትእዛዝ ቢኖር፤ በዚህ “ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ፤” በሚለው ቃል ተጠቅልሎአል።


“አታመንዝር” ያለ እርሱ ራሱ “አትግደል” ብሏል። ባታመነዝር፥ ነገር ግን ብትገድል፥ ሕግ ተላላፊ ሆነሃል።


ሰው የተፈጠረው በእግዚአብሔር አምሳያ ስለ ሆነ፥ ሰውን የሚገድል ሁሉ በሰው እጅ ይሞታል።


እርሱም “የትኞቹን?” አለው። ኢየሱስም እንዲህ አለው “አትግደል፥ አታመንዝር፥ አትስረቅ፥ በሐሰት አትመስክር፥


ትእዛዛትን ታውቃለህ፤ አትግደል፤ አታመንዝር፤ አትስረቅ፤ በሐሰት አትመስክር፤ አታታልል፤ አባትህንና እናትህን አክብር።”


ማናቸውንም ሰው መትቶ የሚገድል ፈጽሞ ይገደል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች