Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘዳግም 4:46 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

46 ሙሴና የእስራኤል ልጆች ከግብጽ ከወጡ በኋላ ድል በነሱት፥ በሐሴቦን ተቀምጦ በነበረው በአሞራውያን ንጉሥ በሴዎን ምድር፥ በቤተፌዖር አንጻር ባለው ሸለቆ በዮርዳኖስ ማዶ ያወጃቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

46 ይህም ከግብጽ በወጡ ጊዜ በሙሴና በእስራኤላውያን ድል በተደረገው፣ በሐሴቦን በነገሠው በአሞራውያን ንጉሥ በሴዎን ምድር፣ ከዮርዳኖስ በስተምሥራቅ በቤተ ፌጎር አጠገብ ባለው ሸለቆ ውስጥ በነበሩበት ጊዜ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

46 እነዚህንም ያወጀው በዮርዳኖስ ማዶ በቤትፔዖር ሸለቆ ፊት ለፊት የአሞራውያን ንጉሥ በነበረው በሐሴቦን በነገሠውና ሙሴና እስራኤላውያን ከግብጽ በወጡ ጊዜ ተዋግተው ባሸነፉት በሲሖን ምድር ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

46 ሙሴና የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከግ​ብፅ ከወጡ በኋላ በመ​ቱት፥ በሐ​ሴ​ቦን ተቀ​ምጦ በነ​በ​ረው በአ​ሞ​ሬ​ዎን ንጉሥ በሴ​ዎን ምድር፥ በቤተ ፌጎር አቅ​ራ​ቢያ ባለው ሸለቆ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘዳግም 4:46
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“እኛም በቤተፌዖር ፊት ለፊት በሸለቆው ውስጥ ተቀመጥን።


እነርሱም የእርሱን ምድርና እንዲሁም በዮርዳኖስ ምሥራቅ የምትገኘውን ባሳንን ይገዛ የነበረውን የሌላውን አሞራዊ ንጉሥ የዖግን ምድር ወረሱ።


በዚያን ጊዜ በዮርዳኖስ ማዶ ከነበሩት ሁለቱ አሞራውያን ነገሥታት እጅ፥ ከአርኖን ሸለቆ ጀምሮ እስከ ሔርሞን ተራራ ድረስ፥ ምድሪቱን ወሰድን።


ከዮርዳኖስ ወዲህ ወደ ምሥራቅ ርስታችን ደርሶናልና እኛ ከዮርዳኖስ ማዶ ከእርሱም ወደዚያ ያለውን ከእነርሱ ጋር ርስት አንወርስም።”


በዮርዳኖስ ማዶ በምድረ በዳ፥ በዓረባ ትይዩ በሆነው ሱፍ ፊት ለፊት፥ በፋራን እና በጦፌልም፥ በላባንም በሐጼሮትም በዲዛሃብም መካከል ሳሉ፥ ሙሴ ለእስራኤል ሁሉ የነገራቸው ቃል ይህ ነው።


ከግብጽ በወጡ ጊዜ ሙሴ ለእስራኤል ልጆች የተናገረው ምስክርና ሥርዓት፥ ሕጎችም እነዚህ ናቸው።


በቤተ ፌጎርም ፊት ለፊት በሞዓብ ምድር በሸለቆው ውስጥ ተቀበረ፤ እስከ ዛሬም ድረስ መቃብሩን ማንም አላወቀም።


ለእርሱም አንድ ሰው በሕይወት እንዳይተርፍ አድርገው እርሱንና ልጆቹን ሕዝቡንም ሁሉ ገደሉ፤ ምድሩንም ወረሱ።


የእስራኤልም ልጆች ያሸነፉአቸው፥ ከአርኖንም ሸለቆ ጀምሮ እስከ አርሞንዔም ተራራ ድረስ በምሥራቅ ያለውን ዓረባ ሁሉ በዮርዳኖስም ማዶ በፀሐይ መውጫ ያለውን አገራቸውን የወረሱአቸው ነገሥታት እነዚህ ናቸው፤


በሰይፍህም በቀሥትህም ሳይሆን በፊታችሁም ተርብ ሰድጄ ሁለቱን የአሞራውያንን ነገሥታት ከፊታችሁ አሳደዳቸው።


“መንግሥታትንና አሕዛብን ሰጠሃቸው፤ የሐሴቦንን ንጉሥ የሴዎንን ምድር፥ የባሳንንም ንጉሥ የዐግን ምድር ወረሱ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች